በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግጭት ምክኒያት ብሔራዊ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ሁኔታዎች እንደሚመቻችላቸው ት/ሚ አስታወቀ

በግጭት ምክኒያት ብሔራዊ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ሁኔታዎች እንደሚመቻችላቸው ት/ሚ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:16 0:00

በግጭት ምክኒያት ብሔራዊ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ሁኔታዎች እንደሚመቻችላቸው ት/ሚ አስታወቀ

በግጭት ምክኒያት ብሔራዊ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ሁኔታዎች እንደሚመቻችላቸው ት/ሚ አስታወቀ።

ለመፈተን ከተመዘገቡት 91.5 በመቶ የሚሆኑት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዛሬ ሀገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና መፈተን መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ትምህርት ሚንስቴር አስታውቋል።

በሀገሪቱ በተከሰተው ግጭት ምክንያት በተወሰኑ ቦታዎች በመደበኛው የፈተና ጊዜ ዛሬ የማይሰጥባቸው አካባቢዎች ከአንድ ወር በኋላ ያለው ሁኔታ ተለይቶ እንደሚሰጥ ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ጦርነት ባለባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ከ33 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደማይቀመጡ የክልሉ ትምሕርት ቢሮ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ለፈተናው የተመዘገቡ ሁሉም ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG