በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው - የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ፌልትማን


በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን

በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ለረጅም ግዜ የኖረው የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ መድረሱን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈሪ ፌልትማን አስታውቀዋል። ፌልትማን ይህን ያሉት ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ተቋም ተገኝተው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሲሆን ጦርነት በሀገሪቱ እየተስፋፋ ባለበት ወቅቱ የሁለቱ ሀገራት ግኙነት ፀንቶ ሊቆይ እንደማይችል ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ግንኙነት መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው - የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ፌልትማን
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:21 0:00

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የሰላም ተቋም ተገኝተውበኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ንግግር በሰሜን ኢትዮጵያ እየተደረገ ባለው ጦርነት ዩናይትድ ስቴትስ ወገኝተኛ አቋምእንዳላት መቆጠሩ ስህተት መሆኑንና በጦርነቱ ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉንም ወገኖች እንደምትቃወም ተናግረዋል።ህወሃት ጦርነቱን ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች መግፋቱና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉምተቀባይነት እንደሌለው በመግለፅ በአስቸኳይ ከክልሎቹ እንዲወጡም ጠይቀዋል።

ፌልትማን አክለው በትግራይ ክልል 900 ሺህ ሰዎች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ጠቅሰው ወደ ክልሉ በየወሩ መግባትየነበረበት ሁለት ሺህ የእርዳታ የጭነት መኪናዎች በኢትዮጵያ መንግስት እንዳይገባ መደረጉና የሰብዓዊ ርዳታ ሰጪድርጅቶች ስራቸውን እንዳይሰሩ መደረጉም ባለስልጣናት ሆን ብለው ሰዎች ርዳታ እንዳያገኙ እያደረጉ መሆኑን ያሳያልብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን ሲመጣ አድርጓቸው በነበሩ የፖሊሲ ለውጦችና የዲሞክራሲመሻሻሎች ምክንያት የዩናይትድ ስቴትስ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በአዲስ መልክ ታድሶ እንደነበር ያስታወሱት ፌልትማንየትራምፕ አስተዳደር በህዳሴ ግድብ ምክንያት ለኢትዮጵያ በሚሰጠው ሰብዓዊ እርዳታ ላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብየባይደን አስተዳደር ማንሳቱን እንደማሳያ ጠቅሰዋል።

ሆኖም በኢትዮጵያ ጦርነቱ እየተባባሰ ባለበት በዚህ ወቅት ግን የሁለቱ ሀገር ግንኙነት ባለበት ሊቀጥል እንደማይችልና፣ለአመታት የዘለቀው ግንኙነታቸውም መስቀለኛ መንገድ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። በዚህም ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ልውውጥ ስምምነት ለመሰረዝ እንዲሁም በጦርነቱ ላይ በተሳተፉት ሁሉም ወገኖች ላይማዕቀብ ለመጣል መዘጋጀቷን በአፅንኦት ተናገዋል።

ፌልትማን አክለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ 'መለስ ዜናዊ ይገዛበት ወደነበረው አገዛዝ መመለስ አለመፈለጉንእናውቃለን፣ ምርጫቸውንም እናከብራለን' ያሉ ሲሆን ህወሃት ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ስልጣን ለመያዝ የሚያደርገውንጥረት እንደሚቃወሙም ተናግረዋል።

ፌልትማንት ከንግግራቸው በኃላ ከሰላም ተቋሙ ፕሬዝዳንት ሊዝ ግራንዴ ጋር ባደረጉት ጥያቄና መልስ ኤርትራበአፍሪካ ቀንድ ሰላም ላይ አፍራሽ ሚና እንዳላት ገልፀው በኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ግጭት እጇን እንድታወጣምአሳስበዋል።

ፊልትማን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት የማያበቃ ከሆነ በመላው ኢትዮጵያ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው 28 ሚሊየንሰዎችን ለአደጋ እንደሚያግልጥ እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች ውስጥ መፈታት የሚገባቸው ችግሮችንም እንደሚያባብስተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG