በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ እና ምዕራቡ ዓለም - የሁለት ምዕራባዊያን ምሁራን አመለካከት


ፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ - የአፍሪካ ቀንድ የደኅንነት ጉዳዮች አጥኚና ካናዳ የሚገኘው ባልሲሊ የውጭ ግንኙነቶች ትምህርት ቤት ዳይሬክተር
ፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ - የአፍሪካ ቀንድ የደኅንነት ጉዳዮች አጥኚና ካናዳ የሚገኘው ባልሲሊ የውጭ ግንኙነቶች ትምህርት ቤት ዳይሬክተር

ለረጅም ጊዜ የምዕራቡ ዓለም ቁልፍ አጋር የነበረችውና ከሰብዓዊ ርዳታ ድርጅቶች ጋር በቅርበት ከመሥራት በተጨማሪ ግዙፍ ቁጥር ያለውን ስደተኛ በማስተናገዷ ስሟን ከፍ አድርገው ሲያነሷት የቆየችው ኢትዮጵያ በሰሜን አካባቢዎቿ፣ በተለይ ትግራይ ውስጥ ከተካሄደው ጦርነት ጋር ተያይዞ ግንኙነቷ እየሻከረ የመጣ ይመስላል።

ይህን ተከትሎ “ምዕራባዊያኑ ማዕቀብ ሊጥሉባትእንደሚችሉ ማስፈራራታቸው አሳሳቢነው” ሲሉ የአፍሪካ ቀንድ የደኅንነት ጉዳዮች አጥኚና ካናዳ የሚገኘው ባልሲሊ የውጭ ግንኙነቶች ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አን ፊትዝዠራልድ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ ላለፉትአሥራ አንድ ወራት እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጎን ለጎን የሚካሄደው የመረጃ ጦርነት በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩንም ፕሮፌሰር ፊትዝዠራልድ አመልክተዋል።

ይህ የግንኙነቶች መሻከር ኢትዮጵያ ከዓለምአቀፉማኅበረሰብ ጋርበሚኖሯት ግንኙነትላይ በሚፈጥራቸው ተፅዕኖዎችናተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ስመኝሽ የቆየ ፕሮፌሰር ፊትዝዠራልድን አወያይታለች።

በሌላ በኩል ወታደራዊ መፍትኄ እንደማይታያቸው ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩትና አሁን በትርፍ ሰዓት በጆርጅ ዋሺንግተን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ዴቭድ ሺን ለቮኦኤ ተናግረዋል።

ዴቪድ ሺን ትላንትከአሜሪካ ድምፅ ጋርበነበራቸው አጭር ቃለ ምልልስ “የኢትዮጵያ መንግሥት እኔብቻ ነኝ ትክክል የሚል ዓይነት አቋም መያዙ ትክክል አይደለም” ሲሉ ተችተዋል።

(ከሁለቱም ጋር በተደረጉት ቃለምልልሶች ላይ የተቀናበረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።)

ኢትዮጵያ እና ምዕራቡ ዓለም - የሁለት ምዕራባዊያን ምሁራን አመለካከት
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:22 0:00


XS
SM
MD
LG