በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከሌሎች የማጠናከሪያ ክትባቶች ጋር የተሻለ ውጤት ይሰጣል” አዲስ ጥናት


ነጠላውን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሰዎች፣ ከፋይዘር ወይም ሞደርና፣ በሚወስዷቸው የማጠናከሪያ ክትባቶች፣ የበለጠ የመከላከል አቅም ሊያገኙ እንደሚችሉ አንድ አዲስ የክሊኒካል የመጀመሪያው ጥናት ውጤት አስታወቀ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጤና ተቋም የተደረገው ጥናት እንዳመለከተው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰንን ክትባት የወሰዱ ሰዎች የሞደርና ማጠናከሪያ ክትባት ከወሰዱ በኋላ የሰውነት የተፈጥሮን መከላከያን አቅማቸው (አንቲቦዲ) 76 ጊዜ እጥፍ አሳድጓል፡፡

ይህ የፋይዘርን የማጠናከሪያ ክትባት ከወሰዱት በኋላ 35 ጊዜ እጥፍ ከሚያደገው የተፈጥሮ መከላከያ ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ የሚበልጥ መሆኑን አሳይቷል፡፡

አጥኚዎቹ ሁለተኛውን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት የወሰዱት የሰውነት የተፈጥሮን መከላከያን አቅማቸው የሚያድገው በአራት እጥፍ ብቻ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ጥናቱ ይፋ የተደረገው፣ የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር፣ አንድ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን እና ሌላ ሁለት የሞደርና ክትባትን እንደማጠናከሪያ ክትባት የመስጠቱን አስፈላጊነት መወሰን ይቻል እንደሆነ ለመነጋገር ፣ የሁለት ቀን ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG