የልብ ቀዶ ጥገና በኢትዮጵያውያን የህክምና ባለሙያዎች መሰጠት በጀመረ ባለፉት በአራት አመታት ውስጥ በየአመቱ እስከመቶ የሚደርሱ የልብ ታማሚዎች በሀገር ውስጥ ያለምንም ወጪ ይታከማሉ። እነዚህን ውስብስብና አስቸጋሪ የቀዶ ህክምና ከሚያከናውኑት ሐኪሞች መካከል አንዱና በኢትዮጵያ የልብ ሕክምና ማዕከል የሚሰሩት ዶክተር ፈቀደ አግዋር እስካሁን በግላቸው 312 ስኬታማ የልብ ቀዶ ጥገና ያከናወኑ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ እጅግ ፈታኝ የነበሩትንና በስኬት የተጠናቀቁ የቀዶ ጥገናዎችን የሚተርክ 'የልብ ጠጋኙ ማስታወሻ' የሚል መፅሀፍ አሳትመዋል። ስመኝሽ የቆየ በመፅሃፉና በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ጥገና አሁን ያለበት ደረጃ ዙሪያ ከዶክተር ፈቀደ ጋር ቆይታ አድርጋለች።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሜይ 23, 2022
"ሕግን ማስከበር መብቶችን በመጣስ መሆን የለበትም” - ኢሰመኮ
-
ሜይ 21, 2022
በአማሮ ልዩ ወረዳ ሁለት አዳጊዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
-
ሜይ 20, 2022
የኢትዮጵያ የነዋይ ዋስትና ሰነዶች ልውውጥ ገበያ ለማቋቋም ሥምምነት ተፈረመ