በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቦኮ ሀራም እንቅስቃሴ በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ


የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ ለነዋሪዎች ገንዘብ እየሰጡ እና በተዋጊነት እየመለመሉ በርካታ ስፍራዎችን እየተቆጣጠሩ መሆኑን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የክፍለ ሀገሩ የማስታወቂያ ኮምሽን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘገበ።

የጦር ሰራዊቱ በጸረ ስምቅ ተዋጊ እንቅስቃሴው ስኬት እያስመዘገበ መሆኑን ሲናገር ቆይቷል። ይሁን እና በብዛት በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የሚንቀሳቀሰው ቦኮ ሃራም ከዋና ከተማዋ ጋር በሚዋሰኑ አካባቢዎች መስፋፋቱ አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል።

ሲሮሮ የሚባል የሰሜን ናይጀር ክፍለ ግዛት አካባቢ አስተዳደር በሰጡት ቃል ባሁኑ ወቅት ታጣቂው ቡድን ቢያንስ ስምንቱ ቀበሌዎች ውስጥ እንደገባ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ቦኮ ሃራም ስሙ ሲተረጎም የምዕራባውያን ትምህርት የተከለከለ ነው የተባለው ቡድን እአአ ከ2009 ጀምሮ ስምቅ ውጊያ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን በቅርብ ጊዜያት ደግሞ የምዕራብ አፍሪካ ክፍለ ግዛት የተባለ ቅርንጫፍ ቡድን ተቀላቅሎታል። በቦኮ ሃራም ውጊያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግምት መሰረት 350 000 የሚሆኑ ሰዎች ተገድለዋል፥ ብዙ ሚሊዮኖች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

XS
SM
MD
LG