No media source currently available
በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለ ኃይማኖት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑና “የህወሓት ታጣቂዎች ፈፅመውብናል” ካሉት ጥቃት እንዳመለጡ የሚናገሩ ነዋሪዎች የህወሓትን ምላሽ እንደማይቀበሉት ተናገሩ። የህወሓት ታጣቂዎች ከነሀሴ 24 ሌሊት አንስቶ ለአምስት ቀናት መቆየታቸውን እና ከዚያም ጥቃቱን እንደፈፀሙባቸው የትኛውም ገለልተኛ የሆነ አካል ወደ መንደራቸው ሄዶ ማጣራት የሚችለው ሃቅ ነው ብለዋል።