በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"መምረጥ መብት ነው" ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንት በዋሽንግተን


“መምረጥ መብት ነው” ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንት በዋሽንግተን
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:12 0:00

“መምረጥ መብት ነው” ሰላማዊ የተቃውሞ ትዕይንት በዋሽንግተን

በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ባላፈው ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲ የመምረጥ መብቶችን እንዲከበሩና እንዲጠበቁ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡

በበርካታዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ክፍለ ግዛቶች፣ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የማህበረሰብ አባላት መራጮችን የሚያፍኑ ህጎች እየወጡ መሆኑን በመጥቀስ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፡፡

የሰልፉ ዋና ዓላማ፣ የምርጫ ህጎች እንዲከበሩ ህግ አውጭዎች ላይ ግፊት ለማድረግ መሆኑን ሰልፈኞቹ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡ በተቃውሞው ከዋሽንግተንና ከተለያዩ ክፍለ ግዛቶች የመጡ ሰልፈኞች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

እለቱ ዶ/ር ማርቱን ሉተር ኪንግ ታሪካዊ ንግግር ያደረጉበት እለት በመሆኑም በርካታ አፍሪካ አሜሪካውያን ተገኝተዋል፡፡

የምንፈልገው ምንድነው?

የመምረጥ መብት ነው

መች ነው የምንፈልገው

“የምንፈልገው አሁኑኑ ነው” ይላል የሰልፈኖቹ መፈክር፡፡

ሰልፈኞቹ ከማለዳው 6 ሰዐት ጀምሮ መሰባሰብ የጀመሩት ዋሽንግተን ዲሲ መክፈርሰን ስኩዌር እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ነው፡፡ ቆይታው በመዝናናት ነበር፡፡

ተሳታፊዎቹ የመጡት ከተለያየ አካባቢ ነው፡፡ ለምሳሌ እኝህ ሰው ቢሊ ሀውስ ይባላሉ፡፡ የመጡት ከክሊቭ ላንድ ኦሃዮ ክፍለ ግዛት ነው፡፡ የመጡበትን ምክንያት ነግረውኛል

“እዚህ ያለነው ለመምረጥ እንድንችል የሚያስችለን ድምጽ እንዲያልፍ ነው፡፡ እንዲያልፉ የምንፈልጋቸው ሁለት ረቂቅ ህጎችም አሉ፡፡”

በሰልፉ የጧት ፕሮግራም ላይ፣ ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍል የመጡ፣ የማህብረሰብ መሪዎችና የተለያዩ ተናጋሪዎች ነበሩ፡፡

ከእነዚህ መካከል ከኒዮርክ የመጡት ኩዊን ጊ አንደኛዋ ናቸው፡፡

ጥቁር አሜሪካዊዋ ኩዊን የመድረክና የፊልም አልባሳት ዲዛይነር ሲሆኑ፣ ጾታቸውን የቀየሩ ማህበረሰብ አባላት መሪ ናቸው፡፡ የሰልፉን ዓለማ በምርጫው ዙሪያ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ከሱም ጋር ተያይዞ በጥቁር አሜሪካዊያን ላይ ስላለው ጭቆና አንስተዋል፡፡ የትግል ጊዜው አሁን ነው ይላሉ!

“እዚህ ያለነው ጊዜው አሁን ስለሆነ ነው፡፡ ትግሉን ለመቀጠል ጊዜው አሁን ነው፡፡ ከመቸውም ጊዜ በላይ ለመብታችን ለመውጣት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ልክ አያቶቻችን ለኛ እንዳደረጉት እኛም መውጣት ያለብን ጊዜ አሁን ነው፡፡ አደራውን ማስተላለፊያ ጊዜያችን ይህ ጊዜ ነው፡፡ እየተዋጋን ያለነው ከነጭ የበላይነት ጋር ነው፡፡ እየተዋጋን ያለነው እኛ እንዳናሸነፍ ከሚፈልግ አካል ጋር ነው፡፡” ብለዋል፡፡

እኝህ ከኒዮርክ የመጡትም ጥቁር አሜሪካዊት ሴትም ያልተሸራረፈ መብት እንደሚፈልጉ ይናገራሉ፡፡

“የመምረጥ መብታችንን ለመካለከል ነው እዚህ ያለሁት፡፡ እዚህ ያለኹት መብታችን ያልተደፈረ ወይም ያልተሸራረፈ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡ እንደ ሰው የጠፋን ወይም የተመደሰስን አይደለንም፡፡ የምንፈልገው እየሆነ ካለው ነገር ጋር ተጋፍጠን በመቆም ከፊታችን ያለው ነገር እንዳይደርስብን ለማድረግ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ስለ አሜሪካ ዴሞክራሲ የተነገረን በትምህርት ቤት የተማርነው ይህ አይደለም በማለት የተናገሩት ሌላዋ የመድረክ ተናጋሪ አክቲቪስት ሉሮድስ ማዲሰን ነበሩ፡፡ በጥቁሮች ላይ የሚደረገውን መድልዎ አያይዘው ተርከዋል

“ሶስተኛ ክፍል እያለሁ አስተማሪያችን ለመስክ ጉብኝት የት መሄድ እንዳለብን ድምጽ እንድሰጥ አድርጋን ነበር፡፡ ያኔ ስታስተምረን የሚፈልጉትን ነገር ለመምረጥ ድምጽ መስጠት ዲሞክራሲ ነው ብላ ነግራን ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በጾታችን የተነሳ መምረጥ አትችሉም አላለችንም፡፡ ቤተሰቦቻችሁ ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ከሌላቸው መምረጥ አትችሉም አላለችንም፡፡ በታሪክ ውስጥ ዴሞክራሲና የመምረጥ መብት ችግር ሲገጥመው የኖረ ነው፡፡ በ1870 የወጣው 15ኛው የህግ መንግስቱ ማሻሻያ ለጥቁሮች የመምረጥ መብት አጎናጽፏል፡፡ በዘር ቀለም ምክን ያት የመምረጥ መብትን መንፈግ እንዳማይገባ ደንግጓል፡፡ የጂም ክሮው ህግ ያደረገው ግን የዚያን ተቃራኒ ነው፡፡ የምርጫ ታክስና ለመምረጥ መክፈልን እንዲሁም ብዙዎቹ መራጮች ችለው የማያልፉት የመጻፍና ማንበብ ፈተና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡”

ማድሰን አክለው ሲናገሩ “ በ1920 የተሻሻለው 19ኛው የህግ መንግሥት ማሻሻያም እንዲሁ የሴቶችን መብት ያጎናጸፈ ነው፡፡ ለዚያ መብት መከበር ብዙ ሴቶች እንዲሁ ተሰልፈውበታ፡፡” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በዚያም ትግል ውስጥ በሚያሳዝን መንገድ ለራሳቸው መብት የታገሉት ነጭ ሴቶች፣ የብዙዎቹ ጥቁሮች ሴቶች መብቶች ከራሳቸው ጋር አንድ አድርገው አልተመለከቱትም፡፡ የጥቁር ሴቶች መብት ትግል አብሮ የተካሄደ ቢሆንም የተካደ ሆኗል፡፡” ብለዋል፡፡

በዚህም ዘመን የተቃውሞ ሰልፉ ዋነኛ ምክንያት መሆኑ የተነገረላቸውን የረቂቅ ህጎች እየጸደቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“ ዛሬ ይህን ንግግር በምናሰማበት በዚች ሰዓት 48 ከፍለ ግዛቶች የመምረጥ መብትን የሚገድቡ ወደ 400 የሚደርሱ የረቂቅ ህጎችን እያወጡ ነው፡፡”

የሰልፉ አዘጋጆችና ማህበራዊ አንቂዎች በድረ ገጾቻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ፣ እነዚህ የጸደቁትም ሆነ የረቀቁት ህጎች ስለሚያግዷቸውም ሆነ ስለሚገድቧቸው የምርጫ መብቶች ዘርዝረዋል፡፡

ከነዚህ ውስጥ በፖስታ ቤት የሚላክን ድምጽን አሰጣጥ ሂደትን መገደብ፣ ከምርጫ ቀን በፊት አስቀድሞ የሚደረጉ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቶችንም መከልከል፣ ከምርጫው ቀናት በፊት ያሉትን የድምጽ መስጫ ሰዓታትና ቀናትን መቀነስ፣ ከሁሉም ፓርቲዎች የተውጣጡ ምርጫውን ሂደት የሚገመግም ቦርድም መከልከል የመሳሰሉት የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

እለቱ ዶ/ር ማርቱን ሉተር ኪንግ ታሪካዊ ንግግር ያደረጉበት እለት በመሆኑንም በርካታ አፍሪካ አሜሪካውያን ተገኝተዋል፡፡ ከጥቁሮች መብት ግንባር ቀደም ታጋዮችም እነ ሬቨረንድ አል ሻርፕተን የተቃውሞ ሰልፉን የመሩ ሲሆን የዶ/ር ማርቲን ሉተር ልጅ ማርቲን ሉተር ኪንግ ሶስተኛም አብረዋቸው ነበሩ፡፡

በ1965 በፌደራል መንግሥቱ የወጣውን የመራጮችን መብቶች የሚጠብቀው ህግን የሚያጠናክር ረቂቅ ህግ በተወካዮቹ ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ውስጥ የወጣ ቢሆንም ሪፐብሊካን በቂ ድጋፍ በማግኘት የህግ መወሰኛውን ምክር ቤት ቀርቦ የመጽደቅ እድሉ አነስተኛ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ረቂቅ ህጉ ባለፈው ዓመት ህይወታቸው ባለፈው በቀድሞ የሲቪል መብቶች ተሟጋችና የምክር ቤት አባል ጆን ሉዊስ ስም የተሰየመ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ጆን ሉዊስ ከነዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር አብረው የታገሉ የጥቁሮችና የሰብአዊ መብት አርበኛ ነበሩ፡፡

XS
SM
MD
LG