የህግ ባለሙያ እና ጠበቃ አብዱልጀባር ሁሴንን አሟሟት በተመለከተ የተለያዩ የሁለት ወገን አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ወንድማቸው አቶ ሱልጣን ሁሴን ተመተው መሞታቸውን ሲናገሩ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ፅህፈት ቤት በበኩሉ በተደረገው ምርመራ የአቶ አብዱልጀባር አስከሬን ላይ የሚታይ ደምም ሆነ ቁስል እንደሌለ የአዳማ ሆስፒታል አረጋግጧል ብሏል። ምንሊክ ሆስፒታል ውጤት ግን እስካሁን እንዳልደረሰ ገልጿል።
የአቶ አብዱልጀባር ወዳጅ የሆኑት እና በአዳማ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ እስፔሻሊስት ህክምና እየተከታተሉ ያሉ ዶ/ር ሆራ እንደተናገሩት የአቶ አብዱልጀባር ሰውነት ላይ ከንፈራቸው አከባቢ ቁስል እና ደም ይታይ ነበር ብለዋል።
የአቶ አብዱልጀባር ወዳጅ የሆኑት እና በአዳማ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ እስፔሻሊስት ህክምና እየተከታተሉ ያሉ ዶ/ር ሆራ እንደተናገሩት የአቶ አብዱልጀባር ሰውነት ላይ ከንፈራቸው አከባቢ ቁስል እና ደም ይታይ ነበር ብለዋል።