በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር አሻቅቧል


በአውሮፓ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር እያሻቀበ መሄዱን ተከትሎ ሌላ የቤት ውስጥ የመቀመጥ ክልከላ እንዳይታወጅ፣ መንግሥታት በተለይ በ20ዎቹና በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል ያሉ ያልተከተቡ ሰዎችን እንዲከተቡ የሚያስገድዱ መንገዶችን እየፈላለጉ ነው።

ፈረንሳይ ባልተከተቡ ሰዎች ላይ ለመጣል ያሰበችውን ክልከላዎችንም ጣሊያና እንግሊዝ ተከትለዋታል። ሆኖም ዕቅዱ በሁለቱም ሀገራት ላይ የመንገድ ላይ ተቃውሞን ቀስቅሷል። በርካታ ወግ አጥባቂ የእንግሊዝ ህግ አውጪዎችም መከተብ እንደመስፈርት የሚቀርብ ከሆነ በዚህ ዓመት መጨረሻ በሚካሄደው የፓርቲያቸው ዓመታዊ ጉባኤ ላለመገኘት እያስፈራሩ ነው።

ያም ሆኖ ግን ጣሊያን ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የስፖርት ስታዲየሞችን፣ ሙዚየሞችን፣ ሲኒማ፣ መዋኛዎችንና የስፖርት መስሪያ ቦታዎችን መጠቀም የሚችሉት የተከተቡ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን የሚገልፅ ክልከላ ባወጀች በ24 ሰዓት ውስጥ ክትባቱን ለመውሰድ ቀጠሮ የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር በ200 ከመቶ መጨመሩን የሮም ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG