በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለሰብዓዊ ረድኤት ሥራ ከአዲስ አበባ መቀሌ በረራ ማድረጉ ታወቀ


WFP
WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ረድኤት ፈላጊዎች በፍጥነት እርዳታ ለማድረስ እንዲያግዘው የአየርበረራ ለማግኘት በጠየቀው መሰረት ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በረራ እንዲያደርግ እንደተፈቀደለትና ቅዳሜ ሐምሌ 10/2013 ዓ.ም በረራማድረጉን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከምስል ጋር አያይዞ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

አያይዞም መንግሥት የእርዳታ ሥራው በተቀላጠፈ መንገድ እንዲደረግ አስፈላጊውን ሁሉ ያመቻቻል ብሏል። በሌላ በኩል በዚሁ ጉዳይ ላይየኢዜአ ምንጮቹን ጠቅሶ ባስነበበው ዘገባ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በተደረገው በረራ በምግብና ስነ-ምግብ አቅርቦት ለሚሳተፉ በክልሉከሚገኙ ወረዳዎች መካከል በ21 ወረዳዎች ለሚሠሩ ሠራተኞች ደመወዝ ፣ ለስራ ማስኬጃ፣ ለምግብ ቁሳቁስ መጫኛና ማውረጃ የሚውልገንዘብ መሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል። አውሮፕላኑም ትላንቱኑ መመለሱን ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG