No media source currently available
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የምግብ አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ መሥራቱንና አሁንም ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል የፌደራል መንግሥቱ ጦር ትግራይን “በጊዜያዊነት” ለቅቆ ሲወጣ 400 ሺ ኩንታልእህል የስርጭት ስራ ከሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ትቶ መውጣቱን ተናግረዋል።