ናትናኤል ታምሩ ትውልድና እድገቱ በባህርር ዳር ከተማ ነው። አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እሸት አካዳሚ በተሰኘ የግልትምህርት ቤትና በጣና ሀይቅ የተማረ ሲሆን ስቲም ሲነርጂ የተሰኘው ተማሪዎችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ለማበረታታየሚሰራው ተቋም የመጀመሪያ ፕሮጀክቱን በባህር ዳር ዩንቨርስቲ አቋቁሞ 100 ተማሪዎችን ለማሰልጠን ሲመለምልከተመረጡት ተማሪዎች መሀክል አንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በዛው ተከታተለ። ይህም ለዛሬ የትምህርት ብቃቱናየቴክኖሎጂ ፈጠራዎች መሰረት እንደሆነ ናትናኤል ይናገራል።
ስቲም ኢትዮጵያ ውስጥ ከተለመደው በክፍል ውስጥ የተገደበ የመማር ማስተማር ዘዴ ለየት ያለና በተግባርና ስራዎችየታገዘ እንዲሁም የፈጠራ ስራዎችን የሚያበረታታ የማስተማሪያ ዘዴዎችን ይከተል እንደነበርም ናትናኤል ይገልፃል።
ናትናኤል ከልጅነቱ ጀምሮ በነበረው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፍቅር ላይ በስቲም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ያገኘውክህሎት ሲጨመርበት ገና የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለ የመጀመሪያው የሆነውን የሞባይሌ ቴክኖሎጂ መስራት ቻለ። ወደ12ኛ ክፍል ሲዛወር ደግሞ ብሄራዊ ሽልማት ያስገኘለትን ስማርት ሃውስ ወይም ከውጪ ያለውን የአየር፣ ሙቀትና ብርሃንሁኔታዎችን እያስተዋለ እራሱን የሚያስካክል ቤት ከጓደኞቹ ጋር በመሆን መፍጠር ቻለ።
ናትናኤል መጀመሪያ የሰራው የስልክ መተግበሪያም በስማርት ቤቱ ላይ ግብዓት ነበር። መተግበሪያው በተለይ አንድሮይድስልኮችን ለሚጠቀሙ ሰዎችም የስልክ አጠቃቀማቸውን የበለጠ የሚያቀል ቴክኖሎጂ ነው።
ናትናኤል አሁን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሁለተኛ አመት የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ ይሁን እንጂ ፍላጎቱኮምፒውተር ሳይንስ ማጥናት ነበር። ባለበት ተቋም ግን ትምህርቱ ባለመሰጠቱ ተቀራራቢውን እያጠና መሆኑንነግሮናል። ሆኖም ከሰሞኑ ደግሞ ናትናኤል ጥሩ ዜና አግኝቷል። በአሜሪካን ሀገር ካሊፎርኒያ ግዛት የሚገኝ ኒቨርቫዩንቨርስቲ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ነፃ የትምህርት እድል ሰጥቶታል። ሆኖም የሚያስፈልጉትን ተጨማሪ ወጪዎችለማሟላት እገዛ እየፈለገ መሆኑን ናትናኤል ይናገራል።
ናትናኤል በስቲም ካገኘው ትምህርት በተጨማሪ ዛሬ ላለው የእውቀት ደረጃም ሆነ ስኬት መሰረቱ ወላጆቹ ያደርጉለትየነበረው ድጋፍና ክትትል እንደሆነም ይገልፃል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ተማሪዎች ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርቶች የበለጠ ፍቅር እንዲኖራቸው በክፍል ውስጥ የሚማሩትትምህርት በአካባቢያቸው ከሚያዩት ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተዛመደ፣ በተግባር የታገዘና ፈጠራን በሚያበረታታ መልኩመሆን ይገባዋል የሚለው ናትናኤል፣ ምኞቱ ባገኘው ነፃ የትምህርት እድል የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተምሮ የሰውንልጆች ህይወት የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎችን ለዓለም ማበርከት ነው።