No media source currently available
የአዲስ አበባ መስተዳድር ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የገዛቸውን የግብርና ግባቶች እና ትራክተሮች ዛሬ ለከተማው አርሶ አደሮች በስጦታ አብርክቷል። አዲስ አበባ ከ27,000 በላይ የተመዘገቡ አርሶ አደሮች እንዳሏት የከተማዋ ግብርና እና አርሶአደሮች ኮምሽን ገልጿል። አንዳንዶቹ ተጠቃሚዎች ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ "አርሶአደሮች ከአዲስ አበባ ከተማ እየተገፉ ነው የኖሩት" ብለዋል።