ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉና እጅግ አነስተኛ የሆነ የጤና ባለሞያ ካለባቸው ሃገራት መሃከል ከቀዳሚዎቹ መሃከል ትመደባለች፡፡ ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህክምና ባለሞያዎች ስራ አጥ እየሆኑ ቅሬታቸውን እያቀርቡ ነው፡፡ ከወራት በፊት በአማራ ክልል የሕክምና ባለሞያዎች የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በዚህ መሰረትም የጤና ሚኒስቴር እና የክልሉ የጤና ቢሮ እስከ ሰኔ 30 ድረስ የሚቆይ የ3 ወራት የስራ እድል አመቻችተው ነበር፡፡ይሁንና የሶስት ወራት ጊዜ እየተጠናቀቀ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ባለሞያዎቹ አሁን ከቀናት በሁላ የኮንትራት ጊዜያቸው ስለሚያልቅ የስራ አጥነት ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡