ዋሺንግተን ዲሲ —
የአፍሪካ ሀገሮች በፍጥነት እየተባባሰ የሚሄድ የኮቪድ-19 ሦስተኛ ማዕበል የተደቀነባቸው መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አሳሰበ።
የኮሮናቫይረስ ስርጭቱ በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን እና በዚህ አካሄዱ በዚህ የአውሮፓ 2021 ዓመተ ምህረት መግቢያ ሁለተኛው የኮቪድ ስርጭት ማዕበል እጅግ አሻቅቦ ከነበረት ይዞታ የባሰ ሊሆን እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ አስታውቋል።
ኮቪድ-19 ወረርሺኝ በአስራ ሁለት የአፍሪካ ሃገሮች ተመልሶ እያንሰራራ መሆኑን ገልጹዋል። መጀመሪያ ላይ ህንድ ውስጥ የተከሰተው ባሁኑ ወቅት “ዴልታ” ተብሎ የሚጠራው እና በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፈው የኮሮ ቫይረስ ዝርያ አስራ አራት የአፍሪካ ሃገሮች መግባቱን የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ ተናግሯል።