በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ስላቅ እና የምፀት ይዘት ያላቸውን የካርቱን ስራዎች በማውጣት የሚታወቀው የካርቱን ስዕል ባለሙያ አለማየሁ ተፈራ ለአመታት የሰራቸውን ስራዎች አሰባስቦ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የካርቱን ስዕሎች ስብስብ የያዘ መፅሃፍ ከሰሞኑ ለገበያ አቅርቧል። ፈንጠዝያ የተሰኘው ይህ መፅሃፍ ከመቶ ሀምሳ በላይ በሆኑ ገፆቹ ወቅታዊና ነባራዊ የሆኑ የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚያነሱ የካርቱን ስራዎች የያዘ ሲሆን በተለይ ወቅታዊ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሁኔታ የሚያሳዩ ስብስቦች እንዳሉት አለማየሁ ይናገራል። በዚህ ስራው ዙሪያ ከአለማየሁ ጋር ቆይታ ያደረገችው ስመኝሽ የቆየ ናት።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ፌብሩወሪ 14, 2025
በሰሜን ጎጃም ጎንጂ ቆለላ ወረዳ 13 መምህራን በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸውን ቤተሰቦች ተናገሩ
-
ፌብሩወሪ 14, 2025
የፕሬዝዳንት ትራምፕ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ርምጃዎች እና ሉላዊ ተጽእኗቸው
-
ፌብሩወሪ 14, 2025
በሲዳማ ከአንድ ቤት ሦስት ህፃናት በቃጠሎ ሞቱ
-
ፌብሩወሪ 13, 2025
ህወሓት ከተፈናቃዮች "በግዳጅ የገንዘብ መዋጮ በመሰብሰብ" አቤቱታ ቀረበበት