በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ማየት የተሳነው ቦይ ስካውት


በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ማየት የተሳነው ቦይ ስካውት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:31 0:00

የአዲስ አበባ ስካውት ማህበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን አይነስውር ስካውት ከዳግማዊ ሚኒሊክ አንደኛ ድረጃ ትምህርት ቤት ለስካውት ለቃለ መሃላ አብቅቷል።። ከተመሰረተ ከመቶ አመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ስካውት ማህበር አባላት የሆኑ የተለያዩ የአካል ጉዳተኞች ያላቸው ስካውቶች ቢኖሩም ማየት የተሳነው አባል ግን ኖሮት እንደማያውቅ የማህበሩ ምክትል ኮሚሽነር ወልጊኛ ሁንዴሳ ነግረውናል።

በአፄ ኃይለስላሴ ሥርዓት ተቋቁሞ ከአንድ መቶ አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ስካውት ማህበር በዚህ ሁሉ እድሜው በአባልነት መዝግቦ የያዘው አንድም ማየት የተሳነው ስካውት አልተገኘም። በዚህም ምክንያት በዳግማዊ ሚኒሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነው ታሪኩ መታፈሪያ የመጀመሪያው ማየት የተሳነው ቦይ ስካውት በመሆን ታሪክ መስራቱን የአዲስ አበባ ስካውት ማህበር ምክትል ኮሚሽነት የሆኑት ወልጊኛ ሁንዴሳ ያስረዳሉ።

ታሪኩ የአይን ብርሃኑን ያጣው ገና የአንድ አመት ከስድስት ወር ህፃን እያለ ወድቆ አጥንት አይኑን በወጋው ወቅት ነው።ይህ ድንገኛ አደጋ ታሪኩን ማየት ቢከለክለውም፣ አይምሮው ግን ብሩህ እንደሆነ፣ በአካባቢውም ሆነ በትምህርት ቤቱራሱን ችሎ የሚንቀሳቀሳቀስ አስደማሚ ልጅ ሆኖ አደገ። ታሪኩ ለዚህ ጥንካሬውና በራስ መተማመኑ ትልቁንመስዋትነት የከፈለችለት እናቱ እንደሆነች ይናገራል።

በአስተሳሰቡ ፈጣንና፣ በትምህርቱም የደረጃ ተማሪ የሆነው ታሪኩ ስካውት የሆነው አስቦበት ሳይሆን በአጋጣሚ ነበር።ወልጊኛ በዳግማዊ ሚኒሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን እያሰለጠኑ ባለበት አጋጣሚ ታሪኩ አይናቸውውስጥ ገባና ስልጠናውን እንዲወስድ አግባቡት።

ታሪኩ ሲናገር አፍ ያስከፍታል፣ ሰው የማሳመን ችሎታውም ከፍተኛ ነው፣ ገና ከልጅነቱም የአመራር ብቃት አለው።የሶስት ወር የስካውት ስልጠናውን ጨርሶ ሲመረቅም የተማሪዎች ዩኒት ሊደርና የአራዳ ክፍለከተማ ስካውት ተጠሪ ሆኖእያገለገለ እንደሆነ ታሪኩ ነግሮኛል።

የስካውት ዋና አላማውም ይህ ነው። ትምህርታዊ የሆነ የሕፃናትና ወጣቶች እንቅስቃሴ የሆነው ስካውት ዋና አላማውወጣቶች በአይምሮ እንዲበለፅጉ፣ በመንፈስ እንዲጠነክሩና በአካል እንዲዳብሩ ብሎም መልካም ዜጋ እንዲሆኑ ማድረግነው። በዘር በሀይማኖት፣ በጎሳና በፆታ ሳይከፋፈል ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር በጎ አመለካከት እንዲኖረው የሚጥረውይህ ማህበር ግን መንግስታት በተፈራረቁ ቁጥር አቅሙ እየተዳከመ በመሄዱ የተፈለገውን ያክል ሳር መስራት እንዳልቻልአቶ ወልጊኛ ያስረዳሉ።

አቶ ወልጊኛ አክለው ስካውት ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ጥቅም ሲያስረዱም የራሱንም የሀገሩንም ሀላፊነት የሚወጣትውልድ ለማፍራት ያስችላል ይላሉ

የታሪኩም ምኞት ይሄ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ልክ እንደሱ በጥሩ ስነ-ምግባር የታነፁና ለሌሎች አርዓያ መሆን የሚችሉ አካል ጉዳተኞችን በማፍራት የተሻለ ትውልድ አካል መሆን ይመኛል።

ከስካውትነቱ በተጨማሪ ታሪኩ ድምፃዊ የመሆን ምኞትም አለው። ከልጅነቱ ጀምሮ በእንጉርጉሮ ያዳበረውን ክህሎትንበባለሙያ ታግዞ ማውጣትም ይመኛል።

አዲስ አበባ ላይ በአሁኑ ሰዓት ማህበራዊ ስራዎች ላይ የሚሳተፉ ከ400 ሺህ በላይ ስካውቶች አሉ። የኮሮና ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ አንስቶም በሽታውን የመከላከያ ግንዛቤ በማስጨበጥ ትልቅ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል። ወልጊኛ እንደነገሩንም በ2020 በመላው ኢትዮጵያ 6 ሚሊዮን ስካውቶችንና 600 አሰልጣኞችን የማፍራት፣ አካል ጉዳተኞችንም የበለጠ የማሳተፍ እቅድ ቢያዝም ከመንግስት ግን ከፍተኛ ድጋፍ ይጠይቃል።

XS
SM
MD
LG