በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ መጀመሪያው አካል ጉዳተኞችን የሚመለከት የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር


አቶ ዳኛቸው ቦጋለ፦ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የአካል ጉዳተኞችን አካታችነት የሚመለከትን የፖለቲካ ክርክር መርተዋል
አቶ ዳኛቸው ቦጋለ፦ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን የአካል ጉዳተኞችን አካታችነት የሚመለከትን የፖለቲካ ክርክር መርተዋል

ከ10 ዓመታት በፊት በዓለም ባንክ እና በዓለም ጤና ድርጅት ትብብር ይፋ የተደረገው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ሪፖርት፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ወደ 20 በመቶ የሚጠጋው ከአካል ጉዳት ጋር እንደሚኖር ይጠቁማል።

ይህ ከፍተኛ የሆነ የስነ ህዝብ ድርሻ የያዘ የማህበረሰብ ክፍል በሀገሪቱ ሁለንተናው እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያለው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ሚና የላቀ መሆኑን ብዙዎቹ ቢስማሙም ሀገሪቱን ለማስተዳዳር የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ አማራጭ ፖሊሲዎችን በልዩ ሁኔታ አቅርበው በአደባባይ ሲከራከሩ ማየት አልተለመደም።

ባሳለፍነው ሳምንት ይሄን የሚቀይር ጅማሮ ተመዝግቧል። አራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የአካል ጉደተኞችን አካታችነት የሚመለከት የፖለቲካ ክርክር አድርገዋል። ለህዝብ በቴሌቭዥን ጭምር በተላለፈው በዚህ ክርክር ላይ ፓርቲዎቹ ለስልጣን ቢበቁ ሊያደርጓቸው የሚችሉ አማራጭ ተግባራትን እና አስተዋውቀዋል።

ክርክሩን የመሩት በአካል ጉዳተኞች መብቶች ላይ የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳኛቸው ቦጋለ ናቸው። አቶ ዳኛቸው ከቪኦኤው ሀብታሙ ስዩም ጋር ባደረጉት ቆይታ ፣ የክርክሩን ይዘት ብሎም በሀገራዊው የኢትዮጵያ ምርጫ ዋዜማ ሊደረጉ ስለሚገቡ አካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ ጉዳዮችን አካፍለዋል።

ሙሉ ቆይታውን እንድታዳምጡ እንጋብዛለን ፦

የመጀመሪያው እንደሆነ ስለተነገረለት አካል ጉዳተኞች ላይ ያነጣጠረ የፖለቲካ ክርክር
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:45 0:00


XS
SM
MD
LG