በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባልደራስ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ


የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ባልደራስ እውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የሕግ ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ፓርቲያቸው ለምርጫ እንዲወዳደሩ በአጩነት ያቀረቧቸውን ተወዳዳሪዎች አልመዘግብም በማለቱ ጉዳዩን ፍርድ ቤት መውሰዳቸውን አስረድተዋል።

በእስር ቤት የሚገኙ ፓለቲከኞች ለመጪው ምርጫ እጩ ሆነው እንዲቀርቡ ከባልደራስ በተጨማሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ በሊቀመንበርነትየሚመሩት የኦሮሞ ነጻነትግንባር (ኦነግ)ም ሲጠይቅ ቆይቷል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ፣ የድጋፍ ፊርማ አሰባሰብ እና መለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 መሰረት በማድረግ በእርስ ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች ለምርጫ ዕጩ ሆነው መቅረብ እንደማይችሉ ያስታወቀ ሲሆን ይህንን ውሳኔ በመቃወም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የወሰደው ባልዳራስ ብቻ ነው።

አቶ ሄኖክ መቼ ወደ ፍርድ ቤትእንደወሰዱት እና ውሳኔውም በምን ቀን እንደሆነ አስረድተዋል።

አቶ ያዕቆብ መኩሪያ፣ አቶ ሙሉሰው ድረስ እና አቶ ፈይሳ በዳዳ የተባሉ ሦስት ዳኞ የተሰየሙበት ችሎት ጉዳዩን በተመለከተ በትላንትናው ዕለትበልዩነት የፍርድ ውሳኔ የሰጠበት ሰነድ እንደሚያሳየው በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ያቀረበውን ባልዳራስን እና ምርጫ ቦርድን ሲያከራክር መቆየቱንጠቅሷል። ባልዳራስ ላቀረበው የይግባኝ ጥያቄ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥበት መታዘዙን እና ቦርዱ መጋቢት 20/2013 ዓ.ም ምላሽ መስጠቱበፍርድ ውሳኔው ላይ ሰፍሯል።

ቦርዱ ይግባኝ ባይ ይግባኙን ማቅረብ ካለበት ጊዜ ያሳለፈ በመሆኑ በይርጋ እንዲታገድለት ከጠየቀ በኋላ ይህ ምላሹ ቢታለፍ በሚል አዋጅናመመሪያን በመጥቀስ አማራጭ ምላሽ ሰጥቷል።

ፓርቲው በአዲስ አበባ ምርጫ ክልሎች ያቀረባቸው ዕጩዎች በሕግ ጥላ ስር ያሉ በመሆናቸው በእጩነት መመዝገብ አይችሉም በመሆኑም የሕግትርጉሙ ወይም በተጠቀሱት አንቀፆች ውስጥ ያለው ሐሳብ በእስር ላይ ያሉ ሰዎች ዕጩ ሆነው መመዝገብ እንደማይችሉ እንደሚደነግግ በመግለፅ ምላሽ ሰጥቷል።

በሁለተኛ አማራጭነትን በሰጠው ምላሽ ደግሞ በእጩነት ከመመዝገብ ተከለከልን የሚል ቅሬታ ያቀረበው ፓርቲ በእጩነት ያቀረባችቸው ዕጩዎች ቦርዱ የምርጫ ሰሌዳ ከማውጣቱ እና የዕጩዎች ምዝገባ ከመጀመሩ በፊት ተከሰው በእስር ላይ ያሉ ሲሆን የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የሚያስከለክል ነው ተብሎ የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ ታስረው የሚገኙ ናቸው። ስለዚህ ግለሰቦቹ እንደልብ ተንቀሳቅሰውመቀስቀስ አይችሉም ይላል። ካለመከሰስ መብት ጋር በተያያዘም ተጨማሪ አንድ መከራከሪ አቅርቧል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ በሁለት ዳንኞች ድምፅ ብልጫ በሰጠው ገዢ ውሳኔ የምርጫ ቦርድን ውሳኔ አፅንቶታል። በፍርድውሳኔውም በእስር ቤት የሚገኙ ሰዎች የመመረጥ መብታቸውን ጨምሮ በርካታ መብቶቻቸው የተገደቡ ናቸው ብለዋል።

በውሳኔ ማጠቃለያቸው ላይም፤ “እስር ላይ የሚገኝ ሰው እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ሕዝብን ለማስተዳደርም ሆነ የፓርቲዎ አጀንዳ ይዞ ሃገሪቱንወደታሰበው ግብ ሊመራ አይችልም። ይህ ደግሞ የምርጫ ዋነኛ ግብ የሆነውን ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር የሚጎዳ እና ይመዝገቡ የተባሉትየይግባኝ ባይ እጪዎች (የባልዳራስ ማለታቸው ነው) በአሁኑ ሰዓት በሌላ ወንጀል ተከሰው የዋስትና መብታቸውን ተከልክለው በማረሚያ ቤትሆነው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ ያሉ ስለሆነ የዕጩነት መብታቸው ተጠብቀው ቢመዘገቡና ቢመረጡ የመረጣቸውን ሕዝብ በእስር ላይ እያሉበነጻነት ተንቀሳቅሰው ሕዝቡን ሊያገለግሉ አይችሉም። ምክኒያቱም መመረጥ ብቻውን አንድን እስረኛ ያለፍርድ ወይም ያለሕጋዊ አሰራር ነፃአያደርገውምና።”

በዳኛ ያዕቆብ መኩሪያ እና በዳኛ ፈይሳ በዳዳ የአብላጫው ውሳኔ የሰጠው ችሎት የተገለፀውን ትንታኔ ካሰፈረ በኋላ ምርጫ ቦርድ የሰጠውንውሳኔ የሚነቅፍበት ምንም ምክኒያት የሌለ መሆኑን በመግለፅ የባልዳራስን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች በእስር ላይመሆናቸው የመመረጥ መብታቸው የሚገድብ ስለሆነ ምርጫ ቦርድ እነርሱን በእጩነት አልመዘግብም ማለቱ ትክክል ነው በማለት መዝገቡንዘግቶታል።

በሌላ በኩል ሐሳባቸውን በልዩነት ያሳፈሩት ዳኛ ሙሉሰው ድረስ፤ የምርጫ ሕጉ በእስር ላይ ያሉ እና የሌሉ ብሎ ክልፍልፋይ አያስቀምጥም ካሉበኋላ፤ ሕጉ በፍርድ ቤት መብቱ የተገፈፈ ነው የሚለው ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉዳይ ላይ እነ አቶ እስክንድር ነጋ መብታቸው በፍርድ የተገፈፈስለመሆኑ ወይም በፍርድ ቤት መብታቸውን ያጡ ስለመሆኑ ምርጫ ቦርድ ምንም ያቀረበው ማስረጃ የለም ብለዋል። ውሳኔያቸውንሲያጠቃልሉም።

“በጥቅሉ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 20/3 በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀፅ 31 እንዲሁም ኢትዮጵያ ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍየሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች የሕግ ክልከላ በሌለበት ሁኔታ መልስ ሰጪ የይግባኝ ባይን ዕጩዎች በሕግ ጥላ ስር የሚገኙ ናቸው በማለትአልመዘግብም በሚል የሰጠው ውሳኔ የሕግ እና የማስረጃ መሰረት የሌለው ስለሆነ ተሽሮ ሊመዘገቡ ይገባል ተብሎ ሊወሰን ሲገባ አብላጫ ድምፅየይግባኝ ባይን አቤቱታ ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ አይደለም በሚል ከሥራ ባልደረቦቼ ሐሳብ ተለይቻለሁ”

የሚፀናው ውሳኔው የአብላጫው በመሆኑ ይግባኙ ውድቅ የተደረገበት ባልደራስ ፓርቲ የሕግ ጠበቃ አቶ ሄኖክ ፓርቲያቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤትውሳኔውን እንዳልተቀበለው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ስድስተኛውን ሃገርዊ ምርጫ በመጪው ግንቦት 28 ለማካናወን ቀነ ቀጠሮ መቁረጡ ይታወቅል።

XS
SM
MD
LG