ባሕር ዳር —
ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍትሀዊ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በንቃት እንደሚሰራ የአማራ ወጣቶች ማኅበር አስታወቀ።
በክልሉ 1.2ሚሊዮን አባላት እንዳለው የገለፀው ማኅበሩ፣ ለምርጫው ሰላማዊ መሆን ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ መዋቅር ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ የማኅበሩ ሊቀ መንበር ገጿል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የባሕር ዳር ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ መኳንንት መከተ በበኩላቸው በቅድመ እና በምርጫ ወቅት እንዲሁም ድህረ ምርጫ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ነው ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡