ዋሽንግተን ዲሲ —
“ታላቅ ህዝባዊ ትዕይንት ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት” የተሰኘ ሰላማዊ ሰልፍ ግንቦት 9/2013 ተካሄዷል።
አስተባባሪዎቹ ሰልፉን ለማሰናዳት ያስፈለገው ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ፣ በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ፣ የሌሎች ሀገራትን ጣልቃ ገብነት ለማውገዝ እንደሆነ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ህዝቦችን ወደ ርስ በርስ ግጭት እያስገቡ ነው ያሏቸውን ቡድኖችን እና ግለሰቦች ከአድራጏታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበቡት ሰልፈኞች ፣ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ነው ያሉትን የሰላማዊ ሰዎች ደህንነት የማስጠበቅ ርምጃም ማጠናከር አለበት ብለዋል።
ይሄ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ መንግስት ለዜጎች በቂ ከለላ ባላደረገበት ሁኔታ ሀገራዊ ምርጫ መደረጉን የነቀፉ፣ በሀገሪቱ ውስጥ እየደረሰ ነው ያሉትን የመብት ጥሰት ያነሳሱ ሌሎች ሰላማዊ ሰልፈኞችም በስፍራው ተገኝተው ነበር። ሀብታሙ ስዩም ፣ የሁሉንም ሀሳብ በቀጣዩ ዘገባው ያስደምጠናል።