በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ማኅበር (ኤንቢኤ) ጋር በመተባበር የሚካሄደው የአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ(ባል) ዕሁድ፤ ግንቦት 8/2013 ዓ.ም. ኪጋሊ ውስጥ ይጀመራል


የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ ሎጎ የተገለጠበት ሥነ ሥርዓት፤ ኪጋሊ የግጥሚያ መድረክ፤ ኪጋሊ፤ ርዋንዳ፤ ታኅሣስ 10/2011 ዓ.ም.
የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ ሎጎ የተገለጠበት ሥነ ሥርዓት፤ ኪጋሊ የግጥሚያ መድረክ፤ ኪጋሊ፤ ርዋንዳ፤ ታኅሣስ 10/2011 ዓ.ም.

የአፍሪካ ቅርጫት ኳስ ሊግ (ባል) በመጀመሪያው ዕቅድ ይጀመራል ተብሎ የታሰበው መጋቢት 4/2012 ዓ.ም. ዳካር፤ ሴኔጋል ላይ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት እንዲተላለፍ ተደርጓል።

ግጥሚያዎቹ የሚካሄዱት በአሜሪካው ብሄራዊ የቅርጫት ኳስ ማኅበር (ኤንቢኤ) እና በዓለምአቀፍ የቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ትብብር ነው።

የ12 የአፍሪካ ሃገሮች፤ የአልጄሪያ፣ የአንጎላ፣ የካመሩን፣ የግብፅ፣ የማዳጋስካር፣ የማሊ፣ የሞሮኮ፣ የሞዛምቢክ፣ የናይጀሪያ፣ የርዋንዳ፣ የሴኔጋል እና የቱኒዝያ ቡድኖች ይሣተፋሉ።

ኤንቢኤ ከሰሜን አሜሪካ ውጭ እንዲህ ዓይነት መርኃግብር ሲያስጀምር ይህ የመጀመሪያው ነው።

ምድብ “ሀ”

ዩኤስ ሞናስቲር (ቱኒዝያ) ኮከብ ተጫዋች - አቴር ማጆክ

ሪቨርስ ሁፐርስ (ናይጀሪያ) ኮከብ ተጫዋች - ቤን ኡዞ

ፔትሪየትስ (ርዋንዳ) ኮከብ ተጫዋች - አሪስቲድ ሙጋቤ

ጂኤንቢሲ (ማዳጋስካር) ኮከብ ተጫዋች - ካምሩን ሪድሌ

ምድብ “ለ”

ፔትሮ ዴ ሉዋንዳ (አንጎላ) ኮከብ ተጫዋች - አቡባካር ጋኩ

ኤኤስ ሳሌ (ሞሮኮ) ኮከብ ተጫዋች - ኤሪክ ኪቢ

ፖሊስ (ማሊ) ኮከብ ተጫዋች - ባድራ ሳማክ

ኤፍኤፒ (ካመሩን) ኮከብ ተጫዋች - ኤባኩ አኩሜንዞ

ምድብ “ሐ”

ዛማሌክ (ግብፅ) ኮከብ ተጫዋች - አናስ ኦሳማ ማህሙድ

ኤኤስ ዱአኔስ(ሴኔጋል) ኮከብ ተጫዋች - ክሪስ ኮክሌ

ጂኤስ ፔትሮሊየርስ (አልጀሪያ) ኮከብ ተጫዋች - ሞሃመድ ሴዲክ ቱአቲ

ፌሮቪአሪዮ ዴ ማፑቶ (ሞዛምቢክ) ኮከብ ተጫዋች - አልቫሮ ካልቮ ማሳ

XS
SM
MD
LG