ዋሽንግተን ዲሲ —
ትናንት አመሻሹን የተከናወነው ፣ “ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር መርሃ ግብር በኢትዮጵያ” የተሰኘው መርሐ- ግብር ፍቅርን ፣ሰላምን ፣አንድነት እና የመከባበር መልዕክቶችን ለማስተላለፍ የተሰናዳ እንደነበረ ከአስተባባሪዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
በመቶ ሺዎች ሚቆጠሩ ሰዎች በጎዳናው ላይ መርሀ ግብር እንደተገኙ እንደሚገመት የተናገሩት ኡስታዝ አቡበከር ቀደም ብሎ መርሐ ግብሩ ከሚከናወንበት ስፍራ ጋር በተገናኘ የተፈጠረው የእስልምና ዕምነት ተከታዮችን “አስከፍቷል” ያሉት ውዝግብ በመነጋገር እንደተፈታም አክለዋል።
ሙሉ መሰናዶውን ያዳምጡ