በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ


የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ጋር በምርጫው ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ መራጩ ህዝብ በተወዳዳሪ ፓርቲዎች ብዛት የሚያጋጥመውን መደነጋገር የሚያስቀርና በጋራ የመስራትን ጠቀሜታ የሚያሳይ ነው ብለዋል ስምምነቱን የተፈራረሙት ፓርቲዎች፡፡

ዛሬ በግዮን ሆቴል የተደረገው የስምምነት ፊርማ ፓርቲዎቹ የፖለቲካ መስመራቸውን ወደ ህዝብ የሚያሰርጹበት፣ ከተፎካካሪነት ወደ አሸናፊነት የሚያሸጋግራቸውን እድል የሚፈጥሩበት እንደሆነ ይናገራሉ የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር ሙሳ አደም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:09 0:00


XS
SM
MD
LG