በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ከሶማሊያ ጋር የሚደረጉ በረራዎችን አቋረጠች


ኬንያ ከሶማሊያ ጋር የሚደረጉ በረራዎችን በሙሉ ማቋረጧ ተገለፀ።

ኬንያ ይህን ያደረገችው ሁለቱ ሃገሮች ለአምስት ወራት ያህል ተቋርጦ የቆየውን የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ባደሱ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው።

የኬንያ የሲስቪል አቪየሽን ባለሥልጣን በሁለቱ ሃገሮች ሀገሮች መካከል የሚደረጉ በረራዎች ጉዳተኞችን ለህክምና ከሚያጓጉዙ በረራዎች እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ረድዔት በረራዎች በስተቀር በሁለቱ ሀገሮች መካከል የሚደረግ በረራ በሙሉ እንደሚቋረጥ ለበረራ አባላት በሙሉ ማስታወቂያ ማሰራጨቱን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የሶማሊያ ባለሥልጣን ገልጸዋል።

ዕገዳው ከዛሬ እአአ ግንቦት 11 ቢያንስ እስከመጪው ነሃሴ ዘጠኝ የሚጸና መሆኑን የቪኦኤ የሶማሊኛ ስርጭት ክፍል ጠቁሟል።

የኬንያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን እርምጃውን የወሰደበትን ምክንያት አልገለጸም። ይሁን እንጂ ውሳኔውን ያወጣው ትናንት ሶማሊያ ከኬንያ ጫት ጭነው የሚጓዙ አውሮፕላኖችን ላይ የጣለችው የቀደመው ውሳኔዋ አሁንም የጸና መሆኑን በድጋሚ ማረጋገጧን ተከትሎ መሆኑ ተጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG