የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ቬርሳቬል የአሜሪካንን ከባድ ኑሮ ተቋቁማ፣ ልጆቿን ከቤት ሆና እያሳደገች ጎን ለጎንበተማረችው የጉዞ ወኪል እና የማማከር ስራ የራሷን ድርጅት ከፍታ መስራት ከጀመረች አራት አመት አስቆጥራለች።
ቬርሳቬል ከንግድ ስራው ጎን ለጎን የሚያስደስታት ከጉዞ ጋር በተያያዘ ለደምበኞቿና ማንኛውንም መረጃ ለሚፈልጉኢትዮጵያውያን በዩቲዩብ አማካኝነት የምትለቃቸው ቪዲዮዎች ናቸው። ሰዎች ከሀገር ሀገር ለመጓዝ ምንያስፈልጋቸዋል? ለጉዞ እንዴት መዘጋጀት ይቻላል? ከሻንጣ ውስጥ መጥፋት የሌለባቸው እቃዎችና ሌሎች ከአየርመንገድ ጋር የተያያዙ ጉዳዎች ለታዳሚዎቿ ከምታደርሳቸው መረጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው።
የኮሮና ወረርሽኝ ዓለም እያስጨነቀ ባለበት በዚህ ወቅት ታዲያ በተለይ በአነስተኛና መለስተኛ የንግድ ተቋማት ላይ ከባድጫና በማስከተሉ ለአራት አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ዘመን የጉዞ ወኪልም ስራውን እንዲያቆም ተገደደ።
የቬርሳቬል ስራ ግን አልተቋረጠም። ቬርሳቬል ከኮቪድ19 ጋር ተያይዞ በጉዞዎች ላይ የተደረጉ አዳዲስ ለውጦችንበተለያዩ ማህበራዊ ድህረገፆች በመጠቀም ማድረስ እንደቀጠለች ትናገራለች።
ቬርሳቬል ለህብረተሰቡ የምታደርሳቸው መረጃዎች በጉዞዎች ላይ ብቻ የተገደቡ አይደሉም። በአሜሪካን አገር የሚኖሩኢትዮጵያውያን ኮቪድ 19 ያደረሰባቸውን ጫናዎች መቋቋም የሚያስችሉ ማንኛውንም መረጃዎች እየሰበሰበች፣ባለሙያዎችን እየጋበዘችና፣ በግል በማማከር አገልግሎቶች ትሰጣለች።
ቬርሳቬል በግሏና በድርጅቷ በኩል እየሰጠችው ባለችው የበጎ ስራ አገልግሎት በርካታ ኢትዮጵያውያን ከነበሩበትአጣብቂኝ እንዲወጡ ሆነዋል። ቤት ኪራይ መክፈል ላቃታቸው፣ ኢንሹራንስ ለተቋረጠባቸው፣ ስራ ላጡና የንግድተቋሞቻቸው ለተዘጉባቸው ከመንግስትና ከተለያዩ አካባቢዎች የሚሰጡ ጥቅማ ጥቅሞችን በመጠቆም፣ አንዳንዴምማመልከቻዎችን እንዲሞሉ በማገዝ መፍትሄ ማምጣት ችላለች።
ለመሆኑ መረጃ በስፋት በሚሰራጭበት አሜሪካን ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአካባቢያሰቸው ስለሚሰጡአገልሎቶች መርጃ በማጣት ለምን ችግር ውስጥ ይወድቃሉ? ለቬርሳቬል ያነሳንላት ጥያቄ ነበር።
ቬርሳቬል በተለያዩ ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ዙሪያ መረጃዎችን አሰባስባ ለህብረተሰቡ ለማድረስየምታደርገው ትግል እሷንም አንዳንዴ ይፈትናታል።
ቬርሳቬል 'ቅንነት ትልቅ ዋጋ አለው' ትላለች። በወረርሽኙ ምክንያት ድርጅቷ ተዘግቶ በቆየበት አንድ አመት ጊዜውስጥም ለህብረተሰቡ መልካም በማድረግ በችግር ወቅት ባህልንና ማህበራዊ እሴትን አለመዘንጋት ዋጋ እንዳለውአሳይታለች። የወረርሽኙ ጫና አልፎ በቅርቡ ወደ ስራ ስትመለስም የድርጅቷ መልካም ስራ ቀድሞ እንደሚጠብቃትእርግጠኛ ናት።