በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በጆርጂያ


ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በጆርጂያ

አስተዳደሩን ከተረከቡ የመጀመሪያቸው አንድ መቶ ቀናት የሞላቸው ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ይህንኑ ምክንያት በማድረግ ጆርጂያ ክፍለ ሃገር የድል ማብሰሪያ ህዝባዊ ስብሰባ አድርገዋል።

ስለአሜሪካ መጻኢ ዕጣ ፈንታ እንደአሁን በተስፋ ተሞልቼ አላውቅም ያሉት ባይደን የዚህም ምክንያቱ አገራችን እንደገና ወደፊት መንቀሳቀስ ስለጀመረች ነው፣ ከፍራቻ ይልቅ ተስፋን፣ ከሃሰት ይልቅ ዕውነትን፣ ከጨለማ ይልቅ ብርሃንን መርጠናል ብለዋል።

ባይደን ንግግራቸውን ያደረጉት አትላንታ ከተማ አቅራቢያ በዲሞክራቲክ ብሄራዊ ኮሚቴ ወጭ በተዘጋጀ የፖለቲካ ህዝባዊ ስብስባ ላይ ነው። ህዝብ በዲሞክራሲ የሚፈልገውን ማግኘት እንደሚችል እናንት አረጋጋጣችኋል ሲሉም አክለዋል።

ጆ ባይደን አትላንታ አቅራቢያ ዱሉት ውስጥ በሚገኝ የኤነርጂ ማዕከል ወደሦስት መቶ አስራ አምስት በሚሆኑ መኪናዎች ሆኖ የተገኘው ታዳሚ ከየመኪናው ጲጵታ በማስጮህ ድጋፉን ገልፆላቸዋል።

ባለፈው ጥር ውር ጆርጂያ ውስጥ ለሁለት የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛ ምክር ቤት መቀመጫዎች በተካሄደው የማጣሪያ ምርጫ ራፋኤል ዎርኖክ እና ጃን አሳፍ ማሸነፋቸው ዲሞክራቶች የፊዴራል መንግሥቱን ሥልጣን በአንድነት እንዲቆጣጠሩ አስችሏል።

ፕሬዚዳንት ባይደንም ዲሞክራቶች በመወሰኛም ምክር ቤቱ ሃማሳ መቀመጫ ማያዛቸውን ተጠቅመው ባለፈው ወር የአንድ ነጥብ ዘጠኝ ትሪሊየን የአሜርካ ማገገሚያ ዕቅዳቸው አንድም ሪፐብሊካን አባል ድጋፍ ሳይሰጠው ሊጸድቅላቸው ችሏል። ዲሞክራቶች የሚቆጣጠሩት የተወካዮች ምክር ቤትም እቅዱን አሳልፎላቸዋል።

ትናንት ቀደም ብሎ በኢሚግሬሽን ህግ አስከባሪዎች በሚፈጸመው እስራት

"ቤተሰቦቻችን እየሞቱብን ነው" በማለት ድምጻቸውን ላሰሙ ጥቂት ሰላማዊ ሰልፈኞች ፕሬዚዳንቱ ቆም ብለው ንግግር ያደረጉ ሲሆን

"በምትሉት እስማማለሁ፣ እየሰራንበት ነው፣ አምስት ቀን ስጡኝ" ብለዋል።

በማስከተልም አሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት እንዲያገኙ በሚሊዮኖች ለተቆጠሩ ዜጎች ማገገሚያ እንዲሰጥ እናደርጋለን ብዬ የገባሁትን ቃል ፈጽሜአለሁ ሲሉ ታዳሚውን አሳስበዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በበኩላቸው ቦልቲሞር ሜሪላንድ በሚገኝ የኮቪድ-19 ክትባት መስጫ ማዕከል ባሰሙት ንግግር የአስተዳደራችን አንድ መቶ ቀናት የአሜሪካውያን ምኞት የተንጸባረቀበት ነው ብለዋል።

እሳቸውና ጆ ባይደን አስተዳደሩን በተረከቡበት ወቅት ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለሥራ አጥነት የተዳረጉብት፥ ትምህርት ቤቶች እና የንግድ ድርጅቶች ተዘግተው ነበር

'ከኮቪድ-19 ባሻገር ደግሞ ዲሞክራሲያችን ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል፣ "ካፒቶላችን በአመጸኞች የተጠቃበት ወቅት ነበር" ብለዋል።

ባይደን እና ሃሪስ ቡድን ያስመዘገቡት ክንዋኔ በመወሰኛው ምክር ቤት የሪፐብሊካኖች መሪውን ብዙም አመርቂ አልሆነም። ሴኔተር ሚች መኮነል

"የዲሞክራቶች አጀንዳ" የተከፋፈለችውን ሃገር ይብሱን በፍጥነት ወደግራ ለመጎተት የሚደረገው ሙከራ አካል ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

XS
SM
MD
LG