No media source currently available
ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ከሀረሪ ክልል ውጪ የሚኖሩ የሀረሪ ብሔረሰብ ተወላጆች በሀረሪ ክልል ምርጫ መሳተፋቸው ህጋዊ መሰረት የለውም ሲል ያስተላለፈውን ውሳኔ በጠቅላይ ፍርድቤት የምርጫ ሂደትና ውጤትን የሚያየው ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውድቅ እንዳደረገው የሀረሪ ብሔራዊ ጉባዔ አስታወቀ። የምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስተት ተቆጥቧል።