በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ውስጥ የረድዔት ድርጅቶች ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ደረሰ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰሜን ናይጄሪያ ውስጥ በሚገኙ የዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅቶች ሦስት ጣቢያዎች ላይ ጥቃት መድረሱን አስታወቀ።

ቅዳሜ ሌሊት ዳማሳክ የምትባለው ከተማ ውስጥ ለተፈጸመው ጥቃት ሃላፊነት የወሰደ የለም። ሆኖም ከቦኮ ሃራም የተገነጠለው ስዋፕ ተብሎ የሚጠራው ቡድን በጥቃቱ አድራሽነት ተጠርጥሯል። ቡድኑ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችን የምትረዱ ናይጄሪያውያን የጥቃት ዒላማ እናደርጋችኋለን ብሎ ሲዝት ቆይቷል።

በቅዳሜው ጥቃት ከተጎዱት ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች አንዱ የሆነው የኖርዌይ የስደተኞች እርዳታ ድርጅት ለሲቪሉ ህዝብ እርዳታ የምናጓጉዝባቸው መኪናዎች ወድመውብናል ሲል አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG