በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የአማራ ማህበራት ያስተባበሩት ሰልፍ ተደረገ


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ማኅበራት ያስተባበሩት ሰልፍ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ተደርጓል።
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ማኅበራት ያስተባበሩት ሰልፍ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ተደርጓል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ማኅበራት ያስተባበሩት ሰልፍ ማክሰኞ መጋቢት 28/2013 ዓም ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ተደርጓል።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት የተደረገው ትዕይንተ - ህዝብ ዓላማው “በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ብሄር የለየ በደል እየደረሰባቸው ነው” ላሏቸው የአማራ ብሄር ተወላጆች ድምፅ ለመሆንና የአሜሪካ መንግሥትም “ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር የለየ ጥቃት እንዲቆም ጣልቃ እንዲገባ ለመጠየቅ” መሆኑን አስተባባሪዎች ገልፀዋል።

“ብሄር ተኮር ጥቃት እንዲስፋፋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስተዋፅዖ አድርገዋል፤ እየተፈፀሙ ላሉት የመብቶች ጥሰቶች ተገቢውን ትኩረት አልሰጡም” ያሏቸውን መንግሥታዊ አካላትና መንግሥታዊ ያልሆኑ የመብቶች ጉዳዮች ተቋማትን ሰልፈኞቹ ኮንነዋል።

ከኢትዮጵያ መንግስት እና ወቃሳ ከቀረበባቸው የመብት ተሟጋች ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ምላሽ የታከለበትን ዘገባ ሀብታሙ ስዩም በመቀጠል ያሰማናል።

በዩናይትድ ስቴትስ የአማራ ማህበራት ያስተባበሩት ሰልፍ ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:11 0:00


XS
SM
MD
LG