No media source currently available
ከ8 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው 5ኛው ዙር የኢትዮጵያ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዛሬ ይፋ ተደርጓል። ለ5ዓመታት የሚቆየውና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከድህነት እንደሚያወጣ የታመነበት ፕሮግራም መንግሥትና አጋሮቹ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ወጭ ያደረጉበት መሆኑን ተገልጿል።