በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ “ተስተማሪ” የወጣቶች ንቃት አገልግሎት


.
.

“ተስተማሪ” የወጣቶችን የአስተሳሳብ ልቅና ለማሳደግ ፣ የፈጠራ አቅማቸውን የሚጨምሩ ስልጠናዎችን ለመስጠት የተቋቋመ አገልግሎት ነው። በአውታሩ ስር ከሚቀርቡ አገልግሎቶች አንዱ “የአዕምሮ ጥላ” የተሰኘው በበይነ መረብ ላይ የሚደመጥ መርሐ-ግብር ወይንም “ፖድካስት” ነው።

በመርሐ- ግብሩ ወጣቶችን ለተሻለ ውሳኔ ሰጪነት የሚያበቁ ሀሳቦች ይስተናገዳሉ።ወደ ሃያ የሚጠጉ ክፍሎች እስከአሁን የተደመጡበትን መርሐ-ግብር አዘጋጅተው በማቅረብ ላይ የሚገኙት አበባ ፋንታሁን እና ካርሎ ኤርቶላ ይባላሉ።

የወጣቶቹን ጅምር ፣የመጪ ዘመን ህልም ብሎም የእስከ አሁን እንቅስቃሴያቸውን ይዘት ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም ከሁለቱ ወጣቶቹ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።

ስለ “ተስተማሪ” የወጣቶች ንቃት አገልግሎት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:49 0:00


XS
SM
MD
LG