No media source currently available
በዚህ ዓመት 250 ሺሕ ሄክታር መሬት በመስኖ ስንዴ እየለማ መሆኑን የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታውቋል። ምርቱ ከውጭ የሚገባውን የስንዴ መጠን በግማሽ እንዲቀንስ እንደሚያደርገው በኢንስቲትዩቱ የመስኖ ስንዴ ፕሮጄክት አስተባባሪ ዶ/ር ዳኒኤል ሙለታ ገልፀዋል። ፕሮጀክቱ አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኛነት እንደሚያላቅቅ፣ የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጮችን እንደሚፈጥርም አስተባባሪው አመልክተዋል።