በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለወጣቱ የለውጥ አቀንቃኝ የማነ ንጉስ ሞት


.
.

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በትግራይ ክልል ውስጥ ሊመጣ የሚገባውን ፖለቲካዊ ለውጥ በማቀንቀን፣ ደረሱ የሚላቸውን በደሎች በማሰማት ይታወቃል -የማነ ንጉስ።

ቅዳሜ አመሻሹን በማህበራዊ መገናኛዎች በኩል የተሰራጩ መረጃዎች ወጣቱ የለውጥ አራማጅ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ ዞን በምትገኘው “ሄዋነ” ከተማ መገደሉን ጠቁመዋል።

የየማነ ንጉስን መገደል ያረጋገጡልን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ የደቡብ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት መለሰ ብስራት፣ ከየማነ ንጉስ በተጨማሪ 5 ሰዎች በዕለቱ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ተናግረዋል። ሶስቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ ሁለቱ ደግሞ ድንገተኛ ተኩስ የከፈቱ ታጣቂዎች መሆናቸውን አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

አቶ መለሰ ብስራት ከክስተቱ በኃላ ጊዜያዊ አጣሪ ቡድን በአስቸኳይ ወደ ስፍራው የተላከ መሆኑን፣ ህብረተሰቡን ከማረጋጋት ተግባር በተጨማሪ የሟቾች አስክሬን ተነስቶ በክብር እንዲያርፍ በቅድሚያ መደረጉን ተናግረዋል ። በመቀጠልም ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጥምረት በመሆን የግድያውን ዝርዝር ሁኔታ አጣርቶ ይፋ የሚያደርግ ቡድን እንደተዋቀረም አውስተዋል። የማነህ ካለው ተቀባይነት አንጻር በአካባቢው ሚሊሺያ ተገደለ ብለው እንደማያስቡ አቶ መለሰ አክለው ተናግረዋል ።

የየማነ ንጉስ «የትግል አጋር » የሆኑት እና “ፈንቅል” የተባለው የወጣቶች ንቅናቄ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ወረደ በበኩላቸው ለየማነ ንጉስ ሞት ተጠያቂ ያደረጉት የቀድሞውን የህወሐት አስተዳደር፣የኢትዮጵያ መንግስት “ጁንታ” በማለት የሚጠራውን ኃይል ነው።

የወጣቱን የለውጥ አራማጅ ግድያ በተመለከተ በፈንቅል በኩል ጣት የተጠቆመበት ህወሐት ወገን እስከ አሁን ድረስ የተሰጠ መግለጫም ሆነ መልስ የለም። ቡድኑ በግድያው ውስጥ ያለውን ሚና የሚያሳይ ገለልተኛ ምርመራም እስከአሁን ድረስ ይፋ አልተደረገም።

ሙሉ ዘገባውን ያዳምጡ ፦

ስለ ወጣቱ የለውጥ አቀንቃኝ የማነ ንጉስ ሞት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:51 0:00


XS
SM
MD
LG