በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊያን ያለፉ መሪዎቻቸውን በዛሬው የፕሬዚዳንት ቀን ይዘክራሉ


(የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ጆርጅ ዋሽንግተን፣ኦማስ ጄፈርሰን፣ቲዎዶር ሩስቬልት እና አብርሃም ሊንከን የሚያሳይ ሃውልት)
(የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ጆርጅ ዋሽንግተን፣ኦማስ ጄፈርሰን፣ቲዎዶር ሩስቬልት እና አብርሃም ሊንከን የሚያሳይ ሃውልት)

በአውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በየዓመቱ በወርሃ የካቲት ሦስተኛ ሰኞ በሚውለው የፕሬዚዳንቶች ቀን አሜሪካዊያን ያለፉ መሪዎቻቸውን በክብር ይዘክራሉ። ቀኑ መከበር የጀመረው የዩናይትድ ስቴትስን የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን ዘወትር ለማስታወስ በሚል ሐሳብ ነበር።

አንዳንዶች በየካቲት 22 ከተወለዱት የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን ጋር ልደት ጋር ተያይዞ እንዲከበር የታሰበው ይህ ቀን በየካቲት 12 የተወለዱትን እና ሃገሪቱን በእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት የመሯትን አብርሃም ሊንከንንም ጨምሮ እንዲታሰብና ቀኑም “የፕሬዚዳንቶች ቀን” እንዲባል ሐሳብ አቀረቡ። ሕግ አውጪዎቹ ደግሞ ይህንን ሐሳብ አጥብቀው በመቃወም ቀኑ የጆርጅ ዋሽንግተን የልደትቀን መባል አለበት ሲሉ ፀኑ። ሆኖም ግን ቀኑ እስካሁንም “የፕሬዚዳንቶች ቀን” በመባል እየተጠራ ይገኛል።

ስለዚህ ዛሬ በዚህ ቀን የፌደራል መንግሥት እና የባንክ ሠራተኞችን ጨምሮ ከሥራ ነፃ ሆነው በዓሉእየተከበረ ይገኛል።

የዩናይትድ ስቴትስን የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን
የዩናይትድ ስቴትስን የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን

ጆርጅ ዋሽንግተን በአሜሪካ አብዮታዊ ጦርነት ውስጥ የሰጡት ጉልህ አመራርና የሃገሪቱ የመጀመሪያው መሪመሆናቸው በሕዝብ ዘንድ የሰፋ ወዳጅነትን አትርፎላቸዋል።

በዚህም “የዩናይትድ ስቴትስ አባት” እየተባሉ ሲጠሩ ኖረዋል። ዛሬም እንደዚያው በመባል ይታወቃሉ። ይህ የሆነው በወቅቱ እጅግ ኃይል በነበረው ጦር ላይ የአሜሪካ ቀኞችን ኃይሎች መርተው ለድል በማብቃታቸውነው።

ዋሽንግተን ቀጥለውም ከእርሳቸው በኋላ የተነሱ ፕሬዚዳንቶች ሁሉ የተከተሉትን የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን አካሄድ ቅርፅ በማስያዝ አርአያ በመሆናቸው በታሪክ እየተዘከሩ ቀጥለዋል።

የፕሬዚዳንቱ ሥልጣን ሥራውን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን የሚያስችለውን ያህል በቂ ችሎታና አቅም ሊኖረው እንደሚገባ ዋሽንግተን ቢያምኑም ፤የንጉሰ ነገስቱን ያህል ፈላጭ ቆራጭነት መሆን እንደሌለበት ግን አስተውለዋል።

ምናልባት ሥልጣን ላይ እያሉ ቢያልፉ ሰው የፕሬዚዳንቱ የዕድሜ ልክ ሹመት ነው ብሎ እንዳያስብም በመስጋት ዋሽንግተን ሁለት የምርጫ ዘመኖችን ካገለገሉ በኋላ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ።

ከዚያ በኋላ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለአራት የምርጫ ዘመናት ከዘለቁት ፍራንክሊን ዴላኖሩዝቬልት በስተቀር ከሁለት ዘመናት በላይ ያገለገለ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የለም።

በ1943 ዓ.ም (በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር) የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀውየሕገመንግሥቱ 13ኛ ማሻሻያ ላይ የፕሬዚዳንቱን አገልግሎት በሁለት ዘመናት ገድቧል። በዚህ ሕገመንግሥት መሠረትም አሜሪካ ፕሬዚዳንቷን በአራት ዓመት አንዴ ትመርጣለች። አንድ ፕሬዚዳንትም ከሁለት ዘመናት በላይ ፕሬዚዳንት መሆን እንዳይችል ተገድቧል።

XS
SM
MD
LG