በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበርካቶችን ህይወት በመረጃ የቀየረች ኢትዮጵያዊት


የበርካቶችን ህይወት በመረጃ የቀየረች ኢትዮጵያዊት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:52 0:00

በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አሜሪካ ሲመጡ ትምህርት የመማር፣ የማደግና ትልቅ ቦታ የመድረስ ህልም ሰንቀው ነው። ነገር ግን ብዙዎች መረጃ ባለማግኘት፣ ወይም ኑሮን ለማሸነፍ በሚደረግ ሩጫ ተጠምደው ያሰቡትን ትምህርት ሳያገኙ ይቀራሉ። ሀምራዊት ተስፋ በአሜሪካ አገር ትምህርት ማግኘት ባለመቻላቸው ተስፋ የቆረጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ትምህርት ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ በማመቻቸት ለአመታት ረድታለች።

ሀምራዊት ተስፋ በሜሪላንድ ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የሞንቶጎምሪ ኮሌጅ፣ የማህበረሰብ ትስስር አገልግሎት ባለሙያ ሆና ለበርካታ አመታት አገልግላለች። ስራዋም በአሜሪካን አገር ከሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚያገናኛት ትናገራለች። ታዲያ ሀምራዊት የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪዋን በማህበረሰብ አገልግሎት ተመርቃ ወደ ስራ አለም ከተቀላቀለችበት ጊዜ አንስቶ ያስተዋለችው፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አሜሪካ ከመጡ በኃላ በትምህርት ራሳቸውን አሳድገው የመስራት ሀይልና አቅም እያላቸው በመረጃ ማጣት ችሎታቸው ተገድቦ ከባድ የኑሮ ውጣ ውረድ እንደሚያሳልፉ ነው።

ነገር ግን ብዙዎች እንደቀላል የማያዩት የአሜሪካን ኑሮ ከባድ የመምሰሉን ያክል በርካታ እድሎች ያሉበት ሀገር አገር መሆኑን ሀምራዊት አገልግሎት ለምትሰጣቸው ኢትዮጵያውያን ዘወትር የምታስረዳው ነው።

ለምሳሌ ሀምራዊት በምትሰራበት የሞንቶጎምሪ ኮሌጅ በተለይ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ሰዎች ከቤታቸው ሆነው ሊማሯቸው የሚችሏቸው ነፃ ትምህርቶችና በርካታ ሙያዎችን መሰልጠን የሚችሉባቸው ነፃ የትምህርት እድሎች እንዳሉ ሀምራዊት ትገልፃለች።

ሀምራዊት ትምህርታቸውን መቀጠል ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን መንገዱን ከማመቻቸት በተጨማሪ፣ ካለፈው አመት ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት በዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂንያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚያገለግል ኢትዮ የቤተሰብ አገልግሎት የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ውስጥ እያገለገለችም ትገኛለች። ተቋሙ በዋናነት የተቋቋመው ማህበረሰቡ እርስ በእርሱ እየተገናኘ እንዲረዳዳ ለማገዝ ሲሆን በተለይ ሴቶች በየሁለት ሳምንቱ እየተገናኙ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩበት ልዩ ፕሮግራሞችንም ያዘጋጃሉ።

በተለይ በኮሮና ምክንያት እቤት ከመዋል ጋር በተያያዘ ብዙ ኢትዮጵያውያን በትዳራቸው፣ በልጆቻቸው እንዲሁም ከራሳቸው ጋር የተያይዙ ችግሮች ይገጥሟቸዋል። ሀምራዊት እንዳስተዋለችውም የተለመደው ማህበራዊ ትስስር በመላላቱም፣ በርካቶች ለአይምሮ ጭንቀት ይዳረጋሉ።

በኢትዮ የቤተሰብ አገልግሎት ምክንያት በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጤና፣ በስደተኛ አገልግሎት፣ ልጅ አስተዳደግና የመሳሰሉ ጉዳዮች ችግራቸውን መጋራት፣ ሀሳብ መለዋወጥ ብሎም የባለሙያ ምክር ማግኘት ችለዋል። ሀምራዊትም ተቋሙ ወደፊት ይበልጥ በጎ ፈቃደኞችን በማሳተፍ የማህበረሰቡን ችግር የመቅረፍ ስራዎችን እነሚቀጥል ነግራናለች።

XS
SM
MD
LG