በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቪኦኤ ስፖርት ፦አጫጭር የስፖርት ዜናዎች


ተከናውኗል።የአሸናፊነት ክብሩም ካንሳስ ሲቲ ቺፍስ የተሰኘው ተቀናቃኙን 31 ለ9 ለረታው ታምፓ ቤይ ባኬነርስ ቡድን ሆኗል።
ተከናውኗል።የአሸናፊነት ክብሩም ካንሳስ ሲቲ ቺፍስ የተሰኘው ተቀናቃኙን 31 ለ9 ለረታው ታምፓ ቤይ ባኬነርስ ቡድን ሆኗል።

የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ፦

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከሰሞኑ ተካሄደዋል። ረቡዕ ጥር 26/2013 በተከናወኑ ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀድያ ሆሳዕና 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል።በሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሲዳማ ቡናን 5 ለ0 አሸንፏል። ሀሙስ ጥር 27/2013 በተደረጉ ጨዋታዎች ጅማ አባ ጅፋር እና ባህርዳር ከተማ 2 ለ 2 - አቻ ሲወጡ ፣ ሰበታ ከተማ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። ዓርብ ጥር 28/2013 በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ሀዋሳ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ ባዶ ለባዶ አቻ ወጥተዋል፣ ፋሲል ከነማ ድሬደዋ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ሳምንቱን ፋሲል ከነማ በ 25 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በ20 እና ሀድያ ሆሳዕና 19 ነጥቦች ይከተላሉ።የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችን ደራጃ አቡበከር ናስር ከኢትዮጵያ ቡና በ14 ጎሎች ይመራል።ሙጂብ ቃሲም ከፋሲል ከነማ 12፣ ጌታነህ ከበደ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በ 7 ጎሎች ይከተላሉ።

ባይደን እና የቶኪዮ ኦሎምፒክ ፦

ለአንድ ዓመት ያህል የተራዘመውን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ክንውንን በተመለከተ የሚሰጥ ማናቸውም ውሳኔ ሳይንስን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት የአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ተናገሩ።

የጃፓን መንግስት እና ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ከስድስት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የኦሎምፒክ ጨዋታዎችን ለማስጀመረ ቃል ገብተዋል። ሆኖም ጨዋታዎቹ የሚከናወኑት በጥብቅ ሁኔታዎች ውስጥ ነው ፤ ተመልካቾች እንዳይገኙ ሊደረግ ይችላልም ተብሏል።

ዌስትውድ ዋን ስፖርት በተሰኘ የራዲዮ መርሐ-ግብር ላይ ሀሳባቸውን ትናንት ያጋሩት ባይደን ጠንክረው ሲሰሩ ለሰነበቱ አትሌቶች ሲባል ውድድሩ ይደረጋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል ።ውድድሩ አይደረግም ብሎ ማሰብን እንደሚጠሉም አክለዋል።

ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር መነጋገራቸውን የጠቀሱት ባይደን -ውድድሩን ማከናወን አደጋ አለው የለውም የሚለው ውሳኔ ሳይንስን መሰረት ማድረግ አለበት ብለው እንደሚያስቡ አስተዋቀዋል። (ዘገባው የሮይተርስ ነው)

ዓመታዊው ብሔራዊ የአሜሪካ እግር ኳስ ሊግ ማጠናቀቂያ ስነ-ስርዓት ተከናወነ

ብሔራዊ የአሜሪካ እግር ኳስ ሊግን ቻምፒዮን ለመለየት የሚደረገው ፣«ሱፐር ቦውል» በመባል የሚጠራው የስፓርት እና መዝናኛ ትርኢት በትናንትናው ዕለት ተከናውኗል።የአሸናፊነት ክብሩም ካንሳስ ሲቲ ቺፍስ የተሰኘው ተቀናቃኙን 31 ለ9 ለረታው ታምፓ ቤይ ባኬነርስ ቡድን ሆኗል።

በተመልካቾች ዘንድ በጉጉት ለሚጠበቀው የመሐል ሰዓት መዝናኛ ትርኢት የተመረጠው ካናዳዊው አቤል ተስፋዬ ዘ ዊክኢንድ ተወዳጅ ሙዚቃዎቹን በልዩ ሁኔታ ቁጥሩ ለተመጠነው ተመልካች አቅርቧል።

በታምፓ ፍሎሪዳ ሬመንድ ጄምስ ስታዲዬም በተደረገው በዚህ ስነ-ስርዓት የ30 ዓመቱ ዘ ዊክንድ፣ የቅርብ ጊዜ መታወቂያው በሆነው ቀይ ኮት ፣ጥቁር ሱሪ እና ጥቁር ሸሚዝ አጊጦ ተወዳጅ የሆኑትን ስታር ቦይ፣ ዘ ሂል፣ ካንት ፊል ማይ ፌስ እና ተጨማሪ ሙዚቃዎችን ተጨዋቷል። በርችት ተኩስ በታጀበው መዝጊያ ላይ ደግሞ “ብላይንዲንግ ላይትስ “ የተሰኘውን ሙዚቃውን ፊታቸው በፋሻ በታሸገ በርካታ ተወዛዋዦች ታጅቦ አቀንቅኗል።

በኮቪድ 19 የጥንቃቄ እርምጃዎች ምክንያት ብሔራዊው የአሜሪካ እግር ኳስ ሊግ ዘንድሮ ዝግጅቱን እንዲታደሙ የፈቀደላቸው ሰዎች ቁጥር 25ሺ ብቻ ነበር። ተጨማሪ 30 ሺ ወንበሮች በሰው ቅርጽ በተሰናዱ የተመልካቾች ምስል የተለጠፈባቸው የወረቀት ሰሌዳዎች እንዲሸፈኑ ተደርጓል።

ከአቤል ተስፋዬ -ዘ ዊክኢንድ በተጨማሪ ወጣቷ ገጣሚ አማንዳ ጎርማን -ሶስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጀግኖችን የዘከረ ግጥም አሰምታለች።

በተያያዘ ዜና የዮናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን የዘንድሮው «ሱፐር ቦውል» ባለድል ታምፓ ቤይ ባኬነርስ ቡድን አባላትን እና ያለፈው የብሔራዊ ቅርጫት ኳስ ማህበር የውድድር አሸናፊ የሆኑትን የሎስ ኤንጅልስ ሌከርስ ቡድን አባላት ወደ ዋይት ሃውስ ቤተ-መንግስት እንደሚጋብዙ ታውቋል።

የኮቪድ 19 ስርጭት በርካታ ሰዎችን ያሳተፈ ዝግጅት በቤተ-መንግስቱ ውስጥ ማሰናዳትን አደገኛ አድርጎታል። ግብዣው የሚከናወነው የጤና ስጋት በማይኖርበት ጊዜ እንደሆነም ተጠቁሟል። (ዘገባው የሮይተርስ ነው)

ዓመታዊው ብሔራዊ የአሜሪካ እግር ኳስ ሊግ ማጠናቀቂያ ስነ-ስርዓት ተከናወነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:20 0:00


XS
SM
MD
LG