ዋሽንግተን ዲሲ —
ከወራት በፊት ጦርነትን ካስተናገዱ የትግራይ ክልል ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው መቐሌ የሚገኘው የመቐሌ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎቹን ከነገ ጀምሮ መቀበል ይጀምራል።
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ በጦርነቱ ምክንያት ለችግር ለተዳረጉ ነዋሪዎች የሚሆኑ ለቀን ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶችን ይዘው እንዲመጡ የሚያበረታታ ዘመቻ ከሰሞኑ ተጀምሯል።
በተማሪዎች ተነሳሽነት እንደተጀመረ ስለተነገረለት ዘመቻ ይዘት ብሎም ዩኒቨርሲቲው በተማሪዎች ቅበላ ዋዜማ በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ሀብታሙ ስዩም በዩኒቨርሲቲው የከተማ ፕላን እና ህንጻ ዲዛይን መምህር የሆኑትን እዮኤል ጉዕሽን አነጋግሯል።እሳቸው በዘመቻው አማካይነት የሚገኘውን ድጋፍ ለመቀበል ብሎም ለሚመለከተው ክፍል ለማሸጋገር የተሰናዱ ተጠሪም ናቸው።
ሙሉ መሰናዶውን ያዳምጡ፦