በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ባይሴ”:- የዕውቀት ፈላጊዎች እና ምሁራን መገናኛ


.
.

ከ10 ዓመታት በፊት ወደ ዮናይትድ ስቴትስ የመጣው ሰይፉ ኃይሌ ቶሎሳ ከእነዚህ ዓመታት አብዛኛውን ያሳለፈው በትምህርት ነው። ሁለተኛ ዲግሪውን ከጨረሰ በኃላ በሀገሪቱ ውስጥ ስራ ለማግኘት ደፋ ቀና በሚልበት ሰዓት ነበር ከተቀጣሪነት ይልቅ ራሱ የሚያስተዳድረው ኩባንያ የመመስረት ሀሳብ ያሸነፈው።

ያ ሀሳብ ተብላልቶ “ባይሴን “ ወለደ። “ባይሴ” ከመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተከታታዮች ድረስ የሚገኙ ዕውቀት ፈላጊዎች እና አስጠኝዎችን ለማገናኘት ያለመ የበይነ መረብ ላይ አውታር ነው። አውታሩ ከዚህ በተጨማሪ የጽህፈት አገልግሎት ፈላጊዎች እና ባለሙያዎች የሚገናኙበት መላ ፈጥሯል። በተለያዩ መስኮች ዕውቀት ያላቸው ምሁራን በቪዲዮ የተዘጋጁ ማስተማሪያዎችን የሚሸጡበት አሰራርም አለው።

አገልግሎቱ ከ170 ሀገራት በላይ ውስጥ እንዲያገለግል ታቅዶ እንደተሰራ የሚናገረው ሰይፉ ኃይሌ ቶሎሳ በዓመታት ውስጥ ሚሊየኖችን የሚጠቅም አማራጭ እንዲሆን እንደሚያልም ለአሜሪካ ድምጽ ተናግሯል።

ሙሉ ቃለ-ምልልሱን ያዳምጡ፦

“ባይሴ”:- የዕውቀት ፈላጊዎች እና ምሁራን መገናኛ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:55 0:00


XS
SM
MD
LG