No media source currently available
ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ምሁራን በኢትዮጵያ ሰላም ሚኒስተር እና በዴስቲኒ ኢትዮጵያ አማካኝነት ለአራት ቀናት ተሰባስበው ታሪክን ከግጭት እና ከሃሰት ትርክቶች በጸዳ ሁኔታ በሳይንሳዊ መንገድ ለመጻፍ ምን መደረግ እንዳለበት መክረዋል፡፡ በተጨማሪም ምሁራኑ ፖለቲከኞች በታሪክ ትምሕርት ላይ የሚያሳድሩትን ጫና ለማስተካከልና በታሪክ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በሳይንሳዊ መንገድ ለመፍታት የታሪክ ምሁራን ማኅበር ለማቋቋም ወስኖ ኮሚቴ መስርቷል፡፡