በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ብሔርተኝነት የሚታይባቸው እና በወከሉት ብሔር ላይ የተበዳይነትን መንፈስ ለማስፈን እየሰሩ መሆኑን የሚያሳይ ጥናት ይፋ ሆነ


‘የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ብሄርተኝነት’ የሚል ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ዲፓርትመንት መምህር በሆኑት በዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ እና በኖርዌይ ኤን ኤል ኤ(NLA) ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የጋዜጠኝነት መምህር ቴሬ ሸዳል ባለፈው ሳምንት ይፋ ተደርጓል፡፡

‘የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ብሄርተኝነት’ የሚል ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ዲፓርትመንት መምህር በሆኑት በዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ እና በኖርዌይ ኤን ኤል ኤ(NLA) ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የጋዜጠኝነት መምህር ቴሬ ሸዳል ባለፈው ሳምንት ይፋ ተደርጓል፡፡ ጥናቱ ከጥር 2011 እስከ ታህሳስ 2012 ዓ.ም በነበረው ወቅት የተሰሩ ዜናዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን በተጨማሪም ከ25 በላይ ዋና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትን እንዲሁም የብዙ ጋዜጠኖችን ቃለመጠይቅ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በጥናቱ መሰረትም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ግጭቶችን ከማብረድ ይልቅ እንደሚሰሩበት የመናኛ ብዙሃን ወገንተኝነት ለአንድ ብሄር የወገነ እና ግጭትን በሚያባብሱ ዘገባዎች ላይ ማተኮራቸው እንዲሁም እና ሆነ ብለው የተበዳይ መንፈስ ለመጫን እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ኤደን ገረመው ከጥናት አድራጊዎቹ መሃከል አንዱ የሆኑተን ዶ/ር ሙላቱ አለማየሁን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡
XS
SM
MD
LG