ዋሽንግተን ዲሲ —
ኢትዮሳት ከ60 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን ማስተናገድ የጀመረ አዲስ የሳተላይት መድረክ ነው።
በኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ማህበር እና ኤስ ኢ ኤስ በተሰኘው የሳተላይት አቅራቢ ድርጅት ትብብር የተዘረጋው የሳተላይት መድረክ ለቴሌቭዥን ጣቢያዎች የተሻለ አማራጭ በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች ደግሞ የስራና ስልጠና ዕድሎችን እንደሰነቀ የኤስ ኢ ኤስ የድርጅቱ የኢትዮጵያ ሽያጭ ዘርፍ ሃላፊ መነን አገኘሁ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ስለ መድረኩ አገልግሎቱ ይዘት እና ፋይዳ ለማወቅ የተደረገውን ቃለምልልስ ያዳምጡ።