በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ልግስና ስለቀናው ትምህርት ቤት


.
.

ከወራት በፊት አክሱማይት አብርሃ ተወልዳ ባደገችበት የጎንደር ከተማ ወደ ሚገኘው የቀይ ዐምባ ትምህርት ቤት ያመራችው ፣ የዕድሜ ጠገቡን ትምህርት ቤት ግድግዳዎች በቀለም ለማፍካት ነበር።

በዚያ ደርሳ ዙሪያ ገባውን የተመለከትችው ወጣት ግን ትምህርት ቤቱ አዲስ ቀለም ሳይሆን አዳዲስ ክፍሎችን የሚፈልግበት የተጎሳቆለ ደረጃ ላይ መድረሱን እንደተረዳች ትናገራለች።

በጉዳዩ ላይ ከባለቤቷ ጋር የመከረችው አክሱማይት ለትምህርት ቤቱ የሚሆኑ ተጨማሪ ክፍሎችን ለመገንባት የሚያስችል የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት በማሰብ፣ ዕቅዷን የማህበራዊ መገናኛ ተከታይ ለሆኑ ኢትዮጵያዊያን አጋራች። በጎ ሀሳቧን የደገፉ በመበራከታቸው ከወራት በኃላ “ቀይ አምባ” ትምህርት ቤት 8 በብሎኬት የተሰሩ ተጨማሪ ክፍሎች ታከሉለት ።

አክሱማይት ባገኘችው መልካም የህዝብ ምላሽ በመበረታት ይመስላል አሁን ላይ ደግሞ የህዝብ ቤተመጽሃፍት ለማስገንባት አዲስ ዘመቻ ጀምራለች።

በምህንድስና ስራ ላይ የተሰማራችው ወጣት ማህበረሰብ ደጋፊ ስለሆኑ ሰሞነኛ ተግባራቶቿ ለሀብታሙ ስዩም አጫውታዋለች።

ሙሉ ቃለ ምልልሱን ያዳምጡ ።

XS
SM
MD
LG