በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ሕዝብን አይወክሉም የተባሉ ስያሜዎች እና ምልክቶች እየተቀየሩ ነው


አማራ ማስሚዲያ/ቲቪ ስክሪን ኮፒ
አማራ ማስሚዲያ/ቲቪ ስክሪን ኮፒ

በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ “የሰማዕታት ኃውልት” ተብሎ በሚጠራው ግቢ ውስጥ “የክልሉንሕዝብ የማይወክልና ማንነቱን የማይገልፅ ነው” ተብሎ የታመነበት ኃውልት በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራር እንዲወገድ በመወሰኑ ባለፈው ቅዳሜ ማስወገዱን የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ገልጿል።

ሌሎችንም ስያሜዎችንና ምልክቶችን የመቀየር እንቅስቃሴ መጀመሩን የባህርዳር ከተማ አስተዳደርአስታውቋል።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በለውጡ ለህዝብ ከገባቸው ቃሎች መካከል “የተሳሳቱ ታሪኮችናትርክቶችን ማረም” የሚል ይገኝበታል። በዚህም መሠረት በዚህ ሣምንት በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ የክልሉን ህዝብ የማይወክልና የማይገልፅ ነው ተብሎ የታመነበትን ስያሜዎችንና ምልክቶችንየመቀየር እንቅስቃሴ መጀመሩን የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ የሰው ህይልና ፋይናንስ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጌትነትአይቼው ገልፀዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በአማራ ክልል ሕዝብን አይወክሉም የተባሉ ስያሜዎች እና ምልክቶች እየተቀየሩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00


XS
SM
MD
LG