በግዙፉ የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ፋይዘር እና የጀርመኑ የሕክምና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባዮ ኢንቴክ በጋራ የሰሩት የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት በአሜሪካን አገር መሰጠት ከጀመረ አንድ ሳምንት አስቆጠረ። በኒዮርክ ፍለ ግዛት Long Island Jewish በተሰኘ የጤና ተቋም ውስጥ የምትሰራዋ ነርስ ሳንድራ ሊንድሴይ የመጀመሪያውን ከቤተ ሙከራ ውጪ የተሰጠውን ክትባት ከወሰደች በኃላም በርካታ የጤና ባለሙያዎችና ሌሎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው የሚሰሩ ባለሙያዎች በቅድሚያ ክትባቱን እየወሰዱ ይገኛሉ። ለመሆኑ የኮቪድ 19 ክትባት አወሳሰድ ምን አይነት ነው? ክትባቱ ከተወሰደ በኃላ የሚኖረው ስሜትስ ምን የምስላል? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ባለፈው ሳምንት ክትባቱን ከወሰዱ የመጀመሪያ የጤና ባለሙያዎች መሃል አንዱ የሆነውንና ኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ቻፕሊን ሆኖ በሽተኞችን የማማከር አገልግሎት የሚሰጠውን ኢታና ጨመዳ ዲሳሳን ጋብዘናል።
ፋይዘር ያመረተውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት የወሰደ ኢትዮጵያዊ የህክምና ባለሙያ
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጁላይ 01, 2022
በኢትዮጵያ ድንበር የተነሳው አለመስማማት ሰፊ ውጥረት ፈጥሯል
-
ጁላይ 01, 2022
የቶሌ ጥቃት ተፈናቃዮች ድጋፍ እየጠየቁ ነው
-
ጁን 30, 2022
በአደራዳሪዎች ጉዳይ የመንግሥትና የህወሓት ውዝግብ
-
ጁን 29, 2022
በደራሼ ምክንያት ባለሥልጣናትና ሌሎችም ታሠሩ