በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በኢትዮጵያዊ ተሰጥኦ አምናለሁ"-የዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂ ውድድሮች አሸናፊ ዶ/ር ውለታ ለማ


.
.

“ዌብ ሰሚት” በያመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የቴክኖሎጂው ዓለም ባለሙያዎች እና አፍቃሪያን የሚሳተፉበት የዓለማችን ግዙፉ ትልቁ ጉባኤ ነው።ዘንድሮ ላይ በጉባኤው ከታደሙ 2500 የቴክኖሎጂ ተቋማት መካካል 700 የሚሆኑት የአዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎቻቸውን በዳኞች ፊት በማቅረብ ተፎካክረዋል።

የዘንድሮው ባለድል ደግሞ ኢትዮጵያዊው ተቋም ላሊበላ ኔትወርክስ ሆኗል።ተቋሙ ለዚህ ድል የበቃው የህክምና መረጃዎችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማደራጀት በሚያስችለው "አባይ ሲ ኤች አር" በተሰኘ ምርቱ አማካኝነት ነው።

የተቋሙ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ከ20 ዓመታት በላይ በጤና መረጃ ስርጭት ላይ በሀገር እና ዓለም አቀፍ ደረጃ ያገለገሉት የተለያዩ ሽልማቶች እና ዕውቅናን ያገኙት ዶ/ር ውለታ ለማ ናቸው። ከዚህ ውድድር ቀደም ባሉት ሳምንታት ከዓላማችን የበይነ መረብ ንግድ ገናናዎች አንዱ ስም በተሰየመው ጃክ ማ ፋውንዴሽን በተዘጋጀው የአፍሪካ ንግድ ጀግኖች ፉክክር ውስጥ ከምርጥ 20 ግለሰቦች መካከል አንዷ ሆነዋል።

በአሁኑ ውድድሩ እናሸንፈለን ብለው እንዳልጠበቁ ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩት ዶ/ር ውለታ ሽልማቱ ተስፋ ያለመቁረጥ ውጤት መሆኑን አውስተዋል።ወጣቶች እና ሴቶች በቴክሎጂው መስክ ይሳካላቸው ዘንድ ሊደረጉ ስለሚገቡ ድጋፎችም መክረዋል።

ባልደረባችን ሀብታሙ ስዩም ውድድሩ ወደ ተካሄደበት ሊዝበን ፖርቹጋል በመደወል ስለ ፈጠራ ስራው ይዘት እና ተያያዥ ጉዳዮች ከዶ/ር ውለታ ጋር ተጨዋውቷል።

XS
SM
MD
LG