በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮሮና ምክንያት በ'ኦንላይን' የሚሰጠው የድህረ ምረቃ ትምህርት


በአዲስ ኮሌጅ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪዋን የምታጠናው የምስራች ስለሺ
በአዲስ ኮሌጅ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪዋን የምታጠናው የምስራች ስለሺ

በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ኢትዮጵያ አብዛኞቹን ትምህርት ቤቶቿን ዘግታ በቆየችባቸው ግዜያት በክፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ የሁለተኛና የሶስተኛ አመት ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሲከታተሉ ቆይተዋል፣ ጥቂቶችም ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ በቅተዋል። ይህ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተካሄደ ያለው በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት ሂደት ምን ይመስላል፣ በትምህርት ጥራቱ ላይስ ያሳደረው ተፅእኖ አለ ወይ ስንል ጠይቀናል።

በኮሮና ምክንያት በ'ኦንላይን' የሚሰጠው የድህረ ምረቃ ትምህርት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:07 0:00

የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ሲረጋገጥና የትምህርት ሚኒስቴር ስርጭቱን ለመግታት ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት ሲወስን፣ በአዲስ ኮሌጅ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ዲግሪዋን የምታጠናው የምስራች ስለሺ፣ ወደ ሶስተኛ አመት ለመሸጋገር ለሚቀራት ፈተና እየተዘጋጀች ነበር።

የኮሮና ወረርሽኝን ስጋት ለመቀነስ በሁሉም ደረጃ ያሉ ትምህርት ተቋማት ላልተወሰነ ግዜ እንዲዘጉ ቢወሰንም፣ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ከቤታቸው ሆነው ትምህርታቸውን በድህረ ገፅ አማካኝነት እንዲከታተሉ የወሰነው ብዙም ሳይዘገይ ነበር። የምስራችን ጨምሮም ወደ 200 ሺህ የሚጠጉ የሁለተኛና የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ይህ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመማር ማስተማር ሂደት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የኢንተርኔት አገልግሎት አለምስፋፋት፣ የመብራት መጥፋት እና ኔት ወርክ መቆራረጥ የመሳሰሉ ብዙ ተግዳሮቶች ቢኖሩትም፣ የምስራች አገልግሎቱን ማግኘት ለቻሉ ግን የተሻለ ሁኔታ ፈጥሯል ትላለች።

በተመሳሳይ ዩንቨርስቲ በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት እና ቴክኖሎጂ ሁለተኛ ማስተርሱን እየተማረ የሚገኘው ኦብሴ ማቲዮስ ግን፣ የድህረ-ገፅ ትምህርቱ፣ ተማሪዎች በክፍል ሆነው ከአስተማሪ ጋር በመገናኘት እና እርስ በርስ ማግኘት የሚችሉትን ተጨማሪ ጥቅም አሳጥቷል ይላል።

የሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ስራቸውን በድህረ ገፅ አማካኝነት ሰረተው ለመመረቅ ከበቁ ተማሪዎች መሃል አንዱ ኪሩቤል አምሳሉ ነው። በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴኮኖሎጂ ዩንቨርስቲ የመካኒካል ኢንጅነር ተማሪ የነበረው ኪሩቤል ትምህርቱ በኮሮና ምክንያት ሳይቋረጥ ማጠናቀቁ ቢያስደስተውም፣ አጠቃላይ ሂደቱን ግን እሳት የማጥፋት ስራ ነው ሲል ይገልፀዋል።

የኪሩቤል የትምህርት ዘርፍ ከክፍል ትምህርት በተጨማሪ በቤተ ሙከራ ውስጥ ምርምሮችን ማካሄድ ይጠይቃል። ዩንቨርስቲዎች ደግሞ ጊዜያዊ የኮሮና ታማሚዎች ማቆያ ሆነ በመቆየታቸው ተማሪዎች የጀመርሯቸውን የምርምር ስራዎች ማጠናቀቅ ካለመቻላቸውም በተጨማሪ፣ ለወጪም እንደዳረጋቸው ኪሩቤል ይገልፃል።

እነዚህ ችግሮች ተደራርበው ኪሩቤል በቴክኖሎጂ አማካኝነት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙትም ሆኑ በድህረ ገፅ ታግዘው እየተመረቁ ያሉ ተማሪዎች የሚያገኙት የትምህርት ጥራት ላይ ተፅእኖ አለው ሲል ይሰጋል።

የከፍተና ትምህርት ተቋማት የድህረ ምረቃ ተማሪዎቻቸውን በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያጠናቀቁ የማድረግ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። የምስራችም የመመርቂያ ስራዋን በድህረ ገፅ አማካኝነት ከአማካሪዋ ጋር እየተገናኘች ለማከናወን እየተዘጋጀች ነው። ብዙዎች ግን በክፍል ውስጥ ከአስተማሪ ጋር በመገናኘት ትምህርት የሚቀጥልበትን ጊዜ ይናፍቃሉ።

XS
SM
MD
LG