በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ በደልን የሚቃወም ትዕይንተ-ህዝብ ተደረገ


.
.

በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ድርጅቶች እና የሲቪክ ማህበራት ያስተባበሩት ትዕይንተ -ህዝብ በትናንትናው ዕለት በዋሺንግተን ዲሲ ካፒታል ሂል አደባባይ ተካሄዷል።

በአማራ ክልል ብሄር ተወላጆች ላይ ደረሰ ያሉትን በደል የዘረዘሩት ተሳታፊዎች “ዘርን በለየ” ጥቃት ውስጥ የተሳተፉ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በዚህ ትዕይንተ ህዝብ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት በተለያየ መንገድ በአማራ ብሄር ላይ ለተከታታሉ እልቂቶች አስተዋጽኦ አድርጓል በሚል ወቀሳ ተሰምቷል።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋ በበኩላቸው እንዲህ ያለው ወቀሳ በተሳሳተ መረጃ ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ጠቁመው፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ቀደም ማንነትን ማዕከል አድርጎ ፣በዋናነት በአማራ ህዝብ ላይ የተደረገ ጭፍጨፋን በተደጋጋሚ አውግዟል፣እጃቸው አለበት የተባሉ ሃይሎች በመማረክ ላይ ናቸው።» ብለዋል።

ሀብታሙ ስዩም ዝርዝር ዘገባውን አሰናድቷል።

XS
SM
MD
LG