No media source currently available
በፌደራል መንግስት እና በህውሃት መሃከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ሽሽተው ወደ ሱዳን የሚዘልቁ ሰዎች ቁጥር እለት እለት እየጨምረ መሆኑ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ከማክሰኞ እለት እስከ ትላንት አርብ ጠዋት ድረስ ባሉት አራት ቀናት ውስጥም ከ14000 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሱዳንን ድንበር አልፈው እንደገቡ የመንግስታቱ ድርጀት የስደተኞች ኮሚሽን ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቋል፡፡